ዶክተር አብይ እና ጎንደር

Habtamu Ayalew – ጠቅላያችን ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ጎንደር አቅንተው ህዝብ እንደሚያወያዩ ዜናውን ማስነገራቸው ይታወቃል።  ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት በሚል ከጠቅላይ ሚኒስተር ጽ/ቤት፤ ከብሔራዊ ደህንነት ቢሮ የሀገር ውስጥ ደህንነት ዲቪዚዬን፤ ከፌደራል ፖሊስ፤ ከመከላከያ ተወከልን ብለው ከኮማንድ ፓስቱ ጋር የተቀናጁ ጎንደር ገብተው ከአቶ በለምነህ መኮንን አስተባባሪነት ከብአዴን ጽ/ቤት መመሪያ እየሰጡ ወደ […]

ኮማንድ ፖስቱን ከጥቅም ውጪ ያደረገው አዲስ የካቢኔ ሹመት

የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ከለቀቁ በኋላ፤ በሚቀጥለው ቀን ጠቅላይ ሚንስትሩ ያልሰበሰበው የሚንስትሮች ምክር ቤት እንደተሰበሰበ በማድረግ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ታወጀ። ከዚህ አዋጅ ጀርባ የነበሩት ዶ/ር ደብረጽዮን፣ የመከላከያ ሚንስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ እና ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ጌታቸው አምባዬ ነበሩ። አዋጁን ካወጡ በኋላ ህጋዊ እውቅና ለመስጠት በሚል፤ ጉዳዩ ወደ ምክር […]

አንዷለም አራጌ የመኪና ስጦታ ተበረከተለት – ”ታስሬ ልጆቼን እንዴት ናችሁ? ብሎ የሚጠይቃቸው አልነበረም”

“ከተፈታሁ በኋላ ሰው ሞልቷል። ታስሬ ግን ልጆቼን እንዴት ናችሁ? ብሎ የሚጠይቃቸው አልነበረም። ባለቤቴን የሚያበረታታት ሰው አልነበረም። አሁን እኔ ስፈታ ሰው ሞልቷል።……”  ስሰማው አመመኝ!

የውጭ ምንዛሪ እጥረት – ከ15-20 አመታት ይዘልቃል

የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ይፈትነው ይዟል። ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ የሹማምንቶቻቸውን የውጭ ጉዞ እና ብክነትን በመቀነስ መፍትሔ ለመሻት ሐሳብ አላቸው። ገንዘባቸውን በውጭ አገራት ያስቀመጡ አሊያም ያሸሹ እንዲመልሱ እስከ መማጸንም ደርሰዋል። የመፍትሔ ሐሳቦቻቸው ለውጥ ያመጡ ይሆን?

“የዲሞክራሲ ጥማት የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ መድረሱን ተመልክቻለሁ” እስክንድር ነጋ

“አሁን የዲሞክራሲ ፍላጎቱ ሕዝብዊ መልክ ይዟል፤ ምሁሩ አካባቢ ያለ ስሜት ብቻ መሆኑ ቀርቶ ታች ድረስ ወርዷል። በሌላ በኩል ደግሞ ኢህአዴግ ራሱም ተለውጧል። በለውጥ ሂደት ውስጥ ነው ያለነው። ጥያቄው ይህ ሂደት በሰላማዊ መልኩ ይቀጥላል ወይንስ ወደብጥብጥ ያመራል የሚል ሲሆን ይህም በቀጥታ ገዥው ፓርቲ ከሚያደርገው ነገር ጋር የሚያያዝ ነው” BBC […]

ሁሉንም ሰዎች ሁሌም ማታለል አይቻልም!

ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ የምርት ገበያውም የሠራተኛ ገበያውም፣ የካፒታል ገበያውም የመሬት ገበያውም መዛባታቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ አውቋል፡፡ የምርት ገበያው ዋጋ ሰው አስመርሯል፡፡ በሠራተኛ ገበያው ውጥንቅት ወጣቱ ትውልድ ሥራ አጥቷል፣ ለራስህ ሥራ ፍጠር፤ አለበለዚያ መሞት ወይም መሰደድ ትችላለህ ተብሏል፡፡

በሞያሌ ህይወት ጠፋ በርካታ ቁስለኞች ሆስፒታል ገብተዋል፣ የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ተወንጅሏል

በቅርቡ በመከላከያ ሰራዊት በደረሰው ጥቃት ከሃዘን ያላገገመችው ሞያሌ በዛሬው እለት የከተማዋን ነዋሪዎች ግራ ያጋባ ጥቃት አስተናግዳለች። ከስፍራው በተገኘ መረጃ አራት ሰዎች ሲሞቱ ከሃምሳ በላይ ቆስለዋል። ጥቃቱ ከተማዋ በመከላከያ ሰራዊት ጥበቃ ስር እያለች መፈጸሙ አንጋጋሪ ሆኗል። 

“ሰላም ከፍ ባለ ድምጽ ተራራ ላይ ወጥቶ በመጥራት አይመጣም”በቀለ ገርባ ለዶ/ር አብይ

” አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ እንዳሉት ሰላም ከፍ ባለ ድምጽ ተራራ ላይ ወጥቶ በመጥራት አይመጣም። ሰላም እንዳይኖር ያደረገው የኢህአዴግ አገዛዝ ነው። ህዝቡማ ምንጊዜም ሰላም ወዳድና ሁሌም ሰላማዊ ነው። ስለዚህ ህዝቡ ለሰላሙ ዘብ ይቁም ብሎ ጥሪ ማድረግ እምብዛም ቦታ የለውም። በመሆኑም እውነተኛ ሰላም እንዲሰፍን ከተፈለገ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጽፈት ቤቱ ተመልሶ […]

ዶ/ር አብይን ለቀቅ!!

የዶ/ር አብይ ወደ ሥልጣን መምጣትና የመጡበት ሂደት የህውሃትን መዳከም ያሳያል እንጂ የወያኔ-ኢህአዴግን ህዳሴ አያሳይም። እንደ እኔ እምነት ወያኔ-ኢህአዴግ የሚታደስም ድርጅት አይመስለኝም። ዶ/ር አብይ ይህን ዘመንኑ የጨረስ ሥርዓት ፍጻሜው ጥንቃቄ የተሞላበት እንዲሆን እና ኢትዮጵያንም ያፋፋማት የለውጥ ምጥ የቀለለ እንዲሆን ያደርጉልን ይሆናል እንጂ ከዛ ያለፈም ተአምር ሊሰሩ የሚችሉ አይመስለኝም።