Advertisements

የቤርሙዳን ትሪያንግል ሚስጥር እንደደረሱበት ተመራማሪዎች ገለፁ

በአትላንቲክ ውቂያኖስ በተለምዶ ‹‹ቤርሙዳ ትሪያንግል›› ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ሚስጥር በመጨረሻ እንደደረሱበት የዘርፉ ተመራማሪዎች አስታወቁ፡፡

በ500 ሺህ ኪሎ ሜትር ስኩዌር የውቂያኖሱ ክልል ላይ የተንጣለለው ይህ አነጋጋሪ ውሃማ  ክልል በተለያዮ ጊዜዎች በርካታ  ቁጥር ያላቸውን አውሮፕላኖች፣ መርከቦች፣ የጦር ጀቶችና ሌሎች ቁሶችን ውጦ በማስቀረት ዱካቸውን አጥፍቶ ለአርጂ እንኳን ወሬው ሳይደረስ እስካሁን ሲያነጋግር የቆየ  ሚስጥር ነበር፡፡

ይህንንም ተከትሎ ተመራማሪዎች ለበርካታ ጊዜያት የጉዳዩን ምንነት ሚስጥር ለመፍታት ሲታትሩ ቆይተው አሁን ላይ በለስ ቀናን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እንደተመራማሪዎቹ ከሀገረ ብሪታኒያ አቅራቢያ በሰሜን ባህር ላይ ስድስት ማዕዘን ቅርጽ ያለው ጉም አልያም ደመና መሳይ አየር ከተመለከቱ በኃላ የቤርሙዳ ትሪያንግልን ሚስጥር መፍታት መቻላቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

ከዚህም ጉም ወይም ደመና ስር ደግሞ በሰዓት 170 ማይል በከፍተኛ ፍጥነት የሚምዘገዘግ ንፋስ እንደሚፈልቅ ከሳተላይት ከተገኘ መረጃ ለማወቅ መቻላቸውን ይናገራሉ ተመራማሪዎቹ ፡፡

ይህም 45 ጫማ ከፍታ ያለው ሰፊ የባህር ሞገድ የሚፈጥር በመሆኑ መርከቦችን የመገልበጥና አውሮፕላኖችን ደግሞ ወደ ውቂያኖሱ የመድፈቅ ከበቂ በላይ አቅም እንዳለው ነው ተመራማሪዎቹ ያረጋገጡት፡፡

በዚህም ምክንያት ታዲያ ተመራማሪዎቹ ይህን ግዙፍ ሀይል የሚያመነጨውን ደመና በግርድፉ ‹‹የአየር ቦንብ›› የሚል ስያሜ አውጥተውለታል፡፡

በቤርሙዳ ትሪያንግል ታሪክ በጉልህ የሚነሳው እ.ኤ.አ 1945 አምስት የአሜሪካ የጦር መርከቦችና ሶስት የነፍስ አዳን አውሮፕላኖች ደብዛቸው መጥፋት መሆኑን የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡

ምንጭ፦ EBC ጥቅምት 11፡2009 … ዴይሊ ስታር

Advertisements

Zaggolenews. የዛጎል ዜና

Editor of zaggolenews.com contact editor - zaggolenews2016@gmail.com

You may also like...

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: