በቆሼ በደረሰው አደጋ ለተጎጂ ቤተሰቦች የቤት መስሪያ ቦታና 1 ሚሊየን ብር ሊሰጣቸው ነው

በቆሼ በደረሰው አደጋ ተጎጂ የሆኑ ቤተሰቦችን በዘላቂነት ለማቋቋም አንድ ሚሊየን ብር የቤት ግምት ካሳን በቤተሰብ ደረጃና የለማ የቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጥ ከስምምነት መደረሱ ተነግሯል።

መጋቢት ሁለት በአዲስ አበባ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የደረሰውን አደጋ ተከትሎ፥ ተጎጂዎችን በጊዜያዊነት የመደገፍና በዘላቂነት የማቋቋም ስራ በህዝቡና በመንግስት በኩል እየተሰራ ይገኛል።

በዘላቂነት ጉዳት የደረሰባቸውን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥም መንግስት፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ ባለሃብቶች እና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ እያደረጉ ይገኛል።

ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም መንግስት በገባው ቃል መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተጎጂዎች ከተውጣጣ ኮሚቴ ጋር ሲወያይ ቆይቷል።

በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ያጡትና የኮሚቴው አባላትም በውይይቱ ሂደት ከስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ውሳኔዎች ከጠበቁት በላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ስምምነቱ የቤት ግምት ካሳ፣ የለማ ምትክ ቦታ ስጦታ (ጀሞ አካባቢ)፣ በአደጋው የተጎዱትን ቤተሰብ መስርተው የሚኖሩ ቤተሰቦችንና ተከራዮችንም የተመለከተ መሆኑንም ገልጸዋል።

አስተዳደሩ ከኮሚቴው ጋር ባደረገው ውይይት፥ በቀጣይ ቤት ተገንብቶ ነዋሪዎቹ ወደ ራሳቸው ቤት እስከሚገቡ ድረስ ህይወታቸውን ለሚገፉበት የኪራይ ቤት ገንዘብ መክፈልንም ያካትታል።

ከዚህ ባለፈም ጉዳት በደረሰባቸው ቤቶች ተከራይ የነበሩ ነዋሪዎች የ10/90 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በኪራይ የሚያገኙ ይሆናል። የኮሚቴ አባላቱ እንዳሉት በአደጋው የወደመው ንብረት ካሳ ጉዳይም በቀጣይ የሚሰራበት ይሆናል።

የከተማ አስተዳደሩ አደጋው ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ በአጭርና ረጅም ጊዜ ተጎጂዎች የሚረዱበት ስልት እና አቅጣጫ ቀይሶ እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።።

በአጭር ጊዜ ተጎጂዎች ባሉበት ቦታ መሰረታዊ ፍላጎቶች የማሟላት ጉዳይ በመንግስትና በህብረተሰቡ እየተሰራ ሲሆን፥ አሁንም በዛው መንገድ እንደቀጠለ ይገኛል።

በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ተጎጂዎች እስካሁን ከ76 ሚሊዮን ብር በላይ ሲሰበሰብ፥ በአይነት የተደረገው ድጋፍ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ደርሷል።

 (ኤፍ ቢ ሲ)

በደመቀ ጌታቸው

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s