ድልድይም ግርግዳም ከድንጋይ ነው የሚሰሩት፡

ሁሉንም መሆን እንችላለን!!
.
ወዳጄ የሚገርም ነገር ልንገርህ ድልድይም ግርግዳም ከድንጋይ ነው የሚሰሩት፡፡ ግን ተግባራቸው ይለያያል ድልድይ አንዱን ከሌላው ሲያገናኝ ግርግዳ ግን አንዱን ከሌላው ይለያል፡፡ እና ምን ለማለት ፈልጌ መሰለህ ፍላጎትህ ሀሳብህ ተሰጥኦህ አልሳካ ቢልህ በፍላጎትህና ባንተ መካከል ያለውን ዶፍ የሚያሳልፍህን ድልድይ ገንባ እንጂ ፍላጎትህን ግርግዳ ሰርተህ አትከልለው፡፡ አስተውል ያሰብከው ካልተሳካ የተስፋ መቁረጥ ግርግዳ ሳይሆን የፅናት ድልድይ ስራ፡፡ አንተ አሁን ያሰብከው ስላልሆነ የተመኘህው ስላልደረሰ የልብህን በር አትዝጋ ዛሬውኑ ተነስ ያሰብከውን ትሆናለህ::
.
ጋዜጠኛ መምህር ሙዚቀኛ ተዋናይ ሰአሊ ኢንጂነር የህግ ባለሞያ …..ሌላም ሌላም ትሆናለህ፡፡ ሰው ሀሳቡን ያክላል ስለዚህ ሀሳብህን አክብረው ውደደው ያኔ እናከብርልሀለን፡፡ ፅናት — ድልድይ ነው
ተስፋ መቁረጥ — ግርግዳ ነው፡፡ ሁለቱም በቃላት ይገነባሉ፡ ፡ አልችልም: አይሆንም: አይሳካም: ከንቱ ነው: የትም አልደርስም፡ እድሜዬ ሔዷል ፡ የሚለውን ግንብ አፍርስና፡፡ ይቻላል፡ ይሳካል፡ የማይሆን ነገር የለም፡ እኔ አሸናፊ ነኝ ብለህ ለውስጥህ ንገረውና ወደስኬትህ በድል ተሻገር፡፡ አንተ አሸናፊ ነህ፡፡ ሀሳብህ የእውነት እመነኝ ይሳካል ሀሳቤ ተራ ነው አትበል፡፡ ዛሬ የምታያቸው ግኝቶች በሙሉ ከዚህ በፊት የአንድ ተራ ሰው ሀሳብ ነበሩ፡፡ .
ዛሬ አለም ተቀበላቸው፡፡ ስለዚህ ይህንን ፅሁፍ ስትጨርስ ለውስጥህ እንዲ በል፡፡ እኔ ድልድይ እንጂ ግርግዳ አልሰራም አሸናፊ ነኝ፡ ያሰብኩት ሁሉ ይሳካል፡ እኔ ሰው ነኝ፡ ሰው አለምን ይቀይራል፡፡ እኔም ከቀያሪዎቹ አንዱ ነኝ በል፡፡
.
መልካም የስኬት ጊዜ ተመኘሁ!!
ሼር በማድረግ ለወዳጅዎ ይጋብዙ

☞ከደራሲያን አለም

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s