አርሰናል የመጀመሪያውን አዲስ ፈራሚ ተጨዋች ይፋ አደረገ

ሻልካን በግራ መስመር ሲያገለግል የነበረው በተከላካይ መስመር የመጫወት፣ እንዲሁም በግራ ክንፍ/ በተለምዶ ተመላላሽ/ በሚባለው ቦታ ይብልጥ ውጤታማ መሆኑንን ገልጿል።
“አርሰናል ከፍተኛ ታሪክ ያለው፣ ከእነ ቲዮሪ ኦነሪና የንስ ሌማን ጀምሮ ከልጅነት የምከታተለው ቡድን ነው። አርሰናል በአውሮፓ የገነን እውቅና ያለው ክለብ በመሆኑ ዛሬ እዚህ በመሆኔ ድስተኛ ነኝ” ሲል ለክለቡ ድረ ገጽ ተናግሯል። አያይዞም ” በሚቻለኝ ሁሉ ከለቡን ለመርዳት ዝግጁ ነኝ። ጥንካሬዬ ስነልቦናዬ ነው። እንደማስበው በግራ መስመር መጫወት በጣም ምቾት ይሰጠኛል። ከሁዋላ ሶስት ተከላካይ በሚሰለፍበት አጨዋወትም ብቁ ነኝ” በማለት አቅሙን የገለጸው አዲሱ የአርሰናል ተጫዋች ሲአድ ኮላሲናክ ነው።
የባስኒያ ሄርዚጎቪኒያ ተከላካይ ካሻልካ በነጻ ዝውውር አርሰናልን መቀላቀሉንና እስከ 2022 መፈረሙን ይፍ ያደረገው የክለቡ ዌብ ሳይት፣ የ23 ዓመቱ አዲስ ፈራሚ ከጁላይ አንድ ጀምሮ የአርሰናልን መለያ ለብሶ ለቅድመ ዝግጅት የሚጫወት መሆኑንን አስታውቋል።
ሻልካም ተጫዋቹ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቦ መልካም ተመኝቶለታል። በቲውተር ሃሳባቸውን የሚገልጹ የአርሰናል ደጋፊዎች ጉልበት ያለው፣ ገና እንደሜው ለጋ የሆነ፣ ክለቡን ረዥም ጊዜ ሊያገለግል የሚችል፣ ነገር ግን ከፍተኛ ብር የወጣበት መሆኑን ጠቁመዋል። 50 ሚሊዮን ፓውንድ ውድ ነው ፤ በጣም ውድ ነው ሲል ንዴቱን የገለጸም አለ። ይሁን እንጂ ዜናውን ይፋ ያደረገው የክለቡ ድረ ገጽ ተጨዋቹ ስለተገዛበት ገንዘብ ብዛት ያለው ነገር የለም። ይልቁኑም በነጻ ዝውውር ተዘዋወረ ሲል ነው ዜናውን ያበሰረው።
በቦታው አዲስ ተጫዋች የመጣበት ሞንሬል ” ለቦታዬ እፋለማለሁ። ባልሁበት ሆኜ ቦታዬን ለማስከበር ጠንክሬ እሰራለሁ ” ሲል ተናግሯል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s