“አልቫሮ ሞራታ በሪያል ማድሪድ ደስተኛ አይደለም” ራይሞን ካልዴሮን

via “አልቫሮ ሞራታ በሪያል ማድሪድ ደስተኛ አይደለም” ራይሞን ካልዴሮን — ኢትዮአዲስ ስፖርት

የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ፕሬዝደንት የነበሩት ራይሞን ካልዴሮን ክርስቲያኖ ሮናልዶ ክለቡን የሚለቅ ከሆነ የእሱን አለመኖር ተከትሎ በመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ የመጫወት ሚና ቢሰጠው እንኳን አልቫሮ ሞራታ በማድሪድ ደስተኛ እንዳልሆነና ክለቡን ለመልቀቅም እንደጓጓ ተናግረዋል።

በዚህ የዝውውር ወቅት የስፔናዊው ስም በተደጋጋሚ ከማን.ዩናይትድ ጋር ሲነሳ ቆይቷል እንዲያውም በ 60 ሚ.ዩሮ ዝውውሩ ሊፈፀም ከጫፍ እንደደረሰ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ሮናልዶ ቤርናቢውን ይለቃል አልያም ይቆያል የሚሉ ጥርጣሬዎች በመኖራቸው በቀጣይ የውድድር ዓመት በሶስት ተጫዋቾች በሚመራው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ሞራታ በቁልፍ ተጫዋችነት ሊሰለፍ እንደሚችል ተገምቷል:: ነገር ግን ካልዴሮ; ሞራታ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንደሚዘዋወርና በዝውውር ሂሳቡም ምክንያት ውሉ ከመፈፀም እንደማይቀር አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

“አልቫሮ ሞራታ በሪያል ማድሪድ ደስተኛ አይደለም” ስለግምታቸው ተጠይቀው ለ ዘ ሰን የሰጡት ምላሽ ነበር:: ” ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ጨዋታዎችን አላደረገም ይህ ስምምነት ግን ለሁሉም ወገኖች ታላቅ ነው።

” ለሞራታ ለማን.ዩናይትድ እና ለሪያል ማድሪድ።በዚህ የውል ስምምነት ሁሉም ደስተኛ ይሆናሉ።” ሲሉ ሀሳባቸውን አጠቃለዋል።

በክለቡ የፈፀመውን ገድል ተከትሎ በደጋፊዎች ዘንድ ታላቅ ክብር የሚሰጠውና ከልብ የሚወደደው ክርስቲያኖ ሮናልዶም በድጋሚ ማን.ዩናይትድን ሊቀላቀል እንደሚችል ካልዴሮን ፍንጭ ሰጥተዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s