ዳኒ አልቬስ ፕሪምየር ሊጉን ሊቀላቀል ከጫፍ ደርሷል

via ዳኒ አልቬስ ፕሪምየር ሊጉን ሊቀላቀል ከጫፍ ደርሷል — ኢትዮአዲስ ስፖርት

የማንችስተር ሲቲው አለቃ ፔፕ ጓርዲዮላ የቀድሞ ተጫዋቹን ዳኒ አልቬስን ወደኢትሃድ ለማምጣት ያደረገው ጥረት ለስኬት መቃረቡን ተከትሎ የሁለቱ ሰዎች ዳግም ጥምረት ከወዲሁ አጓጊ ሆኗል፡፡

ባካሪ ሳኛን ፣ ጋኤል ክሊቺንና ዛባሌታን የሚለቀው ማንችስተር ሲቲ ሁነኛ የመስመር ተከላካይ አሰሳ ላይ የከረመ ሲሆን ለቶተንሐሙ ካይል ዎከር ያቀረበውን ጥያቄ በተጫዋቹ ዋጋ መናር ምክንያት አንስቷል፡፡

ጓርዲዮላም ፊታቸውን ወደብራዚላዊው ምርጥ ያዞሩ ሲሆን ጁቬንቱስ ተጫዋቹን የመሸጥ ፈቃደኝነት ማሳደሩን ተከትሎ ሁለቱ አካላት ለስምምነት መቃረባቸውን ዘ ጋርዲያንን ጨምሮ በርካታ የሚዲያ አካላት ዘግበዋል፡፡

ከአሮጊቷ ጋር አስደናቂ የውድድር አመትን ያሳለፈው አልቬስ ስኩዴቶውንና ኮፓ ኢታልያን ከፍ ማድረግ የቻለ ሲሆን በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግም የፍፃሜ ተፋላሚ መሆን ችሏል፡፡

ጁቬ ከተጫዋቹ ዝውውር የሚፈልገውን 5 ሚልዮን ፓውንድ ለመክፈል ሲቲዎች የተስማሙ ሲሆን ከተጫዋቹም ጋር በግላዊ ጉዳዮች ላይ መስማማት መቻላቸው ተጠቅሷል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s