በአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ እስካሁን ሰባት የወርቅ ሜዳልያዎችን አግኝታለች

በአልጄሪያ እየተካሄደ የሚገኘው የአፍሪካ ከ 20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሶስተኛ ቀኑ ላይ ሲገኝ ኢትዮጵያ ከወዲሁ ሰባት የወርቅ ሜዳልያዎችን ጨምሮ አስራ ስምንት ሜዳልያዎችን ማግኘት ችላለች፡፡

via በአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ እስካሁን ሰባት የወርቅ ሜዳልያዎችን አግኝታለች —

በአልጄሪያ እየተካሄደ የሚገኘው የአፍሪካ ከ 20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሶስተኛ ቀኑ ላይ ሲገኝ ኢትዮጵያ ከወዲሁ ሰባት የወርቅ ሜዳልያዎችን ጨምሮ አስራ ስምንት ሜዳልያዎችን ማግኘት ችላለች፡፡

​ትናንት በተደረጉ የፍፃሜ ውድድሮች በወንዶች 400 ሜትር ወገን ቱቼ የወርቅ ሜዳልያውን ሲያሳካ ኤፍሬም መኮንን ሶስተኛ ሆኖ በመጨረስ የነሀስ ሜዳልያውን እጁ አስገብቷል ፤ በሴቶች 800 ሜትር ፍፃሜ ትዕግስት ከተማ የወርቅ ሜዳልያውን ለአገሯ አምጥታለች፡፡

በ400 ሜትር ሴቶች ፍሬ ህይወት ወንዴና ማህሌት ፍቅሬ አንደኛና ሁለተኛ ሆነው በመጨረስ ወርቅና ብሩን ለኢትዮጵያ ማስመዝገብ የቻሉ ሲሆን በወንዶች 400 ሜትር መሠናክል መርዕድ አለሙ ድል በማድረግ ለአገሩ ተጨማሪ ወርቅ ማምጣት ችሏል፡፡

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የወንዶች 1500 ሜትር ፍፃሜውን ሲያገኝ ኢትዮጵያውያኖቹ የወርቅና የነሐስ ሜዳልያውን ለማንም አላስነኩም ፤ ወልዴ ቱፋና ወሮታው እሸቴ ሁለቱን ሜዳልያዎች ለኢትዮጵያ ያሳኩ ወጣቶች ሆነዋል፡፡

በሌላ ውድድር የ10 ሺህ ሜትር እርምጃ ፍፃሜ ሲካሄድ ዮሐንስ አልጋ ለኢትዮጵያ ወርቅ ያመጣ ሌላኛው አትሌት ሆኗል፡፡

ኢትዮጵያ በዚህ ሻምፒዮና ባለተለመዱ ርቀቶችና መርሃ ግብሮች ውጤቶችን እያስመዘገበች ሲሆን ከነዚህም መካከል በ100 ሜትር ሴቶች ኤቢሴ ከበደ የነሐስ ሜዳልያ ፣ እንዲሁም በስሉስ ዝላይ አጁዳ ኡመድ የብር ሜዳልያን ማግኘት ችለዋል፡፡

ከትናንት በስተያ በውድድሩ የመጀመሪያ ቀን በተካሄዱ መርሃ ግብሮች በሴቶች 3000 ሜትር የተወዳደረችው መሰሉ በርሄ ሶስተኛ በመውጣት ነሐስ ያገኘች ሲሆን በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል  ታከለ ንጋቱና ተስፋዬ ድሪባ አንደኛና ሁለተኛ በመውጣት ድል አድርገዋል ፡፡

በአጠቃላይ እስካሁን በተደረጉ የሻምፒዮናው ፍፃሜዎች ኢትዮጵያ 7 ወርቅ 4 ብርና 7 ነሐስ በማስመዝገብ የደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ተቀምጣለች ፤ ሻምፒዮናው ዛሬም በተለያዩ የውድድር መርሃ ግብሮች ቀጥሎ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s