ሳዑዲ አዋጇን በሰላሳ ቀን አራዘመች

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ኢትዮጵያ የምህረት አዋጁ እንዲራዘም ያቀረበችውን ጥያቄ ተከትሎ አዋጁን ማራዘሙ ተነግሯል። የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ የሌላቸው የሌሎች ሀገራት ዜጎች በ90 ቀናት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ያስቀመጠው የምህረት አዋጅ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም መጠናቀቁ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ መንግስትም የተጠናቀቀው የእፎይታ ጊዜ ይራዘም ዘንድ ከሳዑዲ መንግስት ጋር በዲፕሎማሲያዊ መስመር ሲነጋገር ነበር። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ መልዕክት በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በኩል ለሳዑዲ ንጉስ ከተላከ በኋላ አሁን ላይ ፍሬ አፍርቷል።

ይህም ለኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ይናገራሉ። ቃል አቀባዩ የቀነ ገደቡ መጨመር ሰፊ ቁጥር ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ እድል የሚሰጥና የተሻለ ስራ መስራት የሚያስችል በመሆኑ፥ በዚያ ያሉ ዜጎች እድሉን ሊጠቀሙበት ይገባል ብለዋል።

በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር አሚን አብዱል ቃድር በበኩላቸው፥ ቀነ ገደቡን በመጠቀም በተለይም የጉዞ ሰነድ ወስደው በመጠባበቅ ላይ ያሉትን በአስቸኳይ ለማስወጣት ከቀደመው ልምድ በመነሳት እንደሚሰራ ተናግረዋል። አምባሳደር አሚን ከዚህ ቀደም የጉዞ ሰነድ የወሰዱ ኢትዮጵያውያን በዚህ እድል ቀዳሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑም አሳስበዋል።

እስካሁን ምንም አይነት የጉዞ ሰነድ ያልወሰዱ ብዙ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የሳዑዲ ዓረቢያ ክፍሎች በመኖራቸው ተጨማሪውን የምህረት ጊዜ በአግባቡ እንዲጠቀሙም ጠይቀዋል። የምህረት አዋጁ በ90 ቀናቱ በተለያዩ ምክንያቶች መውጣት ያልቻሉት የሁሉም ሀገራት ዜጎች በሰላም ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ በማሰብ ለአንድ ወር መራዘሙን የሳዑዲ የፓስፖርት ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አስታውቋል።

ጭማሪው ካለፈው እሁድ ሰኔ 18 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ እንደዋለ ታውቋል። በእስካሁኑ ሂደት 111 ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የጉዞ ሰነድ ቢወስዱም የተመለሱት ግን 45 ሺህ ያህል ብቻ ናቸው።

አብዛኛው ዜጎች በመጨረሻ ሰዓት ላይ ለመመለስ በመወሰናቸው በትራንስፖርት ላይ እጥረት በመፈጠሩና የአውሮፕላን ጣቢያዎች መጨናነቅ፥ ዜጎችን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ መፍጠሩን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s