ወታደራዊ ሚስጥር ለሻዕቢያ አቀብሏል የተባለውና ከሳውዲ ተይዞ የተከሰሰው ግለሰብ ተፈረደበት

በሀገር ክህደት እና የመንግስትን ንብረት በመዝረፍ ወንጀል የተከሰሱ ሶስት ግለሰቦች በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ። የትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ እንደገለፀው የእስራት ቅጣት ከተወሰነባቸው ግለሰቦች መካከል፤

ላለፉት ስምንት ዓመታት የሃገሪቱን ወታደራዊ ሚስጥር ለኤርትራ መንግስት አሳልፎ ሲሰጥ ቆይቷል የተባለ ተከሳሽ ይገኝበታል። ገብረህይወት ገብረጊዮርጊስ የተባለው ግለሰብ በሳዑዲ ዓረቢያ ተሰውሮ ከቆየ በኋላ፥ በኢትዮጵያ የፀጥታ ሀይሎች ጥብቅ ክትትል ተይዞ ወደ ሃገር እንዲመጣ መደረጉንም ቢሮው ገልጿል፡፡

ወንጀለኛው በስልክ እና ደብዳቤ ልውውጥ የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላትና ጦር መሳሪያን በፎቶግራፍ በማስደገፍ ለሻዕቢያ ሰላዮች አሳልፎ ሲሰጥ መቆየቱም ተነግሯል።  ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የአድዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰሞኑን በዋለው ችሎት ግለሰቡ በሰባት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

ከተከዜ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ሃይል 10 ሺህ ብር ግምት ያለው ኦፕቲክ ፋይበር ሰርቆ የተከሰሰው ገብረሊባኖስ ታመነ የተባለ ተከሳሽ እና ተባባሪው ግለሰብም በሶስት እና ስድስት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት ተቀጥተዋል።

ኢዜአ

.

ምንጭ፦ ኢዜአ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s