የሰላም ባስ ጋራዥ የቦንብ ጥቃት ደረሰበት ተባለ

Related image

አዲስ አበባ የሚገኘው የሰላም አውቶቡስ ጋራዥ ላይ የቦንብ ጥቃት መፈጸሙን ኢሳት አስታወቀ። ጥቃቱ የተፈጸመው ሃሙስ ምሽት ነው ተብሏል። ለጥቃቱ ሃላፊነቱን የወሰደ አካል አለመኖሩም ተዘግቧል። ይሁን እንጂ ከመንግስት ወገንም ሆነ የሰላም አውቶቡስ ባለንብርት ከሆነው የህወሃት ኩባንያ ጉዳቱን አስመልክቶ የተባለ ነገር የለም።

ኢሳት ” ታማኝ ምንጮቼ ነገሩኝ” ሲል እንደዘገበው ጥቃቱ የተፈጸመው ባልታወቁ አካላት ሲሆን፣ የደረሰው የጉዳት መጠን አልተገለጸም። ምስክሮች እንደተናገሩት ተከታታይ ፍንዳታዎችና የተኩስ ድምጽ ተደምጧል። ኢሳት ” ሰበር” ሲል ባወጀው ዜና መረጃዎች አሰባስቦ እንደገና በዘገባው እንደሚመለስበት አመልክቷል።

አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎችም በደፈናው ጥቃት መፈጸሙን ከመናገራቸው በላይ ዝርዝር ያሉት ነገር የለም። በአማራ ክልል ተከስቶ በነበረው አመጽ የሰላም ባስ መቃጠሉ፣ እንዲሁም በኦሮሚያ መሰባበሩ ይታወሳል። አሁን አሁን ከሚነሱ ተቃውሞዎች ጋር በተያያዘ የድርጅት ንብረት እየመረጡ ማጥቃት የተልመደ ሆኗል።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s