በአወዳይ ከፍተኛ እልቂት ደረሰ፤ ሶማሊያና ኦሮሚያ ወደከፋ ግጭት እያመሩ ነው፤ ሶማሌ ክልል የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንትን በዘር ፍጅት ከሰሰ

 

dis 2በኢትዮጵያ ሶማሊያና በኦሮሚያ ክልል በድንበር መቆራቆስ የተጀመረው ግጭት እየተካረረ ሄዶ በአወዳይ እልቂት መፈጸሙ ተሰማ። የሁለቱም ክልሎች የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች በቁጥር ባይስማሙም እልቂት ስለመፈጸሙ ማስተባበያ አላቀረቡም። የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዲሱ 12 የሶማሌ ክልል ተወላጆች ፣ 6 ከኦሮሚያ ህይወታቸው ማለፉን አስታውቀዋል። የሶማሌ ክልል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ በበኩላቸው ቁጥሩን ያሻቅባሉ። ነዋሪዎች እንደሚሉት እልቂቱ የከፋ ነው። የሶማሌ ክልል የኦሮሚያን ክልል በዘር ፍጅት ሲከስ ቁጥራቸው ከ600 የሚበልጡ ሰዎች ምርፈናቀላቸው ተመልክቷል።

” ማንም ይፍረድ ” ሲሉ 213 ሲገደሉ 41 ቆስለዋል። 300 ሰዎችን ለመግደል ሲወሰዱ መከላከያ ደርሶ እንዳዳናቸው የሶማሌ ክልል የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ ለቪኦኤ ይናገራሉ። በትናንትናው እለት አወዳይ ላይ 30 ሰዎች ሞተው አስከሬናቸውን ክልሉ እንደተረከበ ተናግረዋል። ሃያ አስከሬን ገና ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

ቀደም ሲል  የጉርሱም ወረዳ የፀጥታ ምክትል ኃላፊ የነበሩና አቶ መሐመድ አብዱራህማን የሚባሉ የቀድሞ አስተዳዳሪ  አቶ ሰላን መሐመድ፣ እንዲሁም የኦሮምያ አድማ በታኝ ፖሊስ አባል የነበረ አብዱጀባር የሚባል ወጣት ወደ ሃረር እየተጓዙ ሣሉ የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ይዘዋቸው ሌሊት እሥር ቤት ውስጥ ካሣደሯቸው በኋላ ሁለቱም መገደላቸውን ተከትሎ ህዝብ ቁጣ ውስጥ መግባቱን  አቶ አዲሱ ያስረዳሉ። በዚህ ሳቢያ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች ከተደረጉት ሰላማዊ ሰልፎች መካከል በአወዳይ ሰልፉ ወደ ግጭት አምርቶ ከላይ የተገለጸው የእርስ በርስ መጨራረስ እንዳስከተለ ያስረዱት አቶ አዲሱ፣ የሶማሌ ክልል የኮሙኒኬሽን ጉዳይ ጽህፈት ቤት ሃላፊን ” ብቃት የሌላቸው፣ ስሜታዊና የክልላቸውን ሳይሆን የራሳቸውን ስሜት የሚናገሩ፣ የተናገሩት ሁሉ የሚያስከሣቸው ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

የሶማሌ ክልል የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢንጂነር ኢድሪስ ኢስማኤል እንደሚሉት በሁሉም የኦሮሚያ ክልል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳን ጨመሮ በስም በመጥራት በዘር ማጥፋት እንደሚወነጀሉ አስታውቀዋል። አቶ አዲሱ ለዚህ ምላሽ ሲሰጡ የቀረበውን ክስ የልጅ ዓይነት ንግግር አድረገው ነው የወሰዱት። ይልቁኑም ማን ምን፣ ለምንና እንዴት እየሰራ እንደሆነ ሁሉም ያውቃል፣ ሚዲያውም በቂ ግንዛቤ አለው ብለዋል።

አሳዛኙ ጉዳይ ሰለሞን አባተ ያናገራቸው ሰው የተናገሩት ነው። መከለከያ ሰራዊት ባለበት ካምፕ ውስጥ እየተቀጠቀጥን በፈቃደኛነት ክልሉን ለቀን እንደወጣን እንድንናገርና ቪዲዮ እንድንቀረጽ ተጠይቀናል ሲሉ መደመጣቸው ነው። በዚሁ ሳቢያ ሁለት ሰዎች በድብደባ ሞተዋል። ንብረታችን እየተዘረፈ መሆኑንን ጠቅሰው በፈቃዳቸው ነው የወጡት በሚል የሶማሌ ክልል የሰጠውን መግለጫ እርቃኑን አውጥተዋል።

21 ሰዎች በሃይል እንዲፈናቀሉ ተፈርዶባቸዋል። ሙሉውን ዘገባ ከመጨረሻው አካባቢ ያድምጡ

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s