ዜና ፎቶ – የጎሳ ፖለቲካና ጥጣው – የጎሳ ፖለቲካ አክተሮች ይህ ያስደስታችኋል?

ለመመልከት የሚከብዱትን ምስሎች ለማተም አልፈቀድንም። የከፋ ግድያና አረመኔነት የተመላበት ርምጃ ሲወሰድ የሚያሳዩ ምስሎች ቢኖሩም ከጥቅማቸው ጉዳታቸው ስለሚበዛ ትተናቸዋል። በተመሳሳይ ሁሉም ሚዲያዎች ሌሎችን እልህ ውስጥ የሚከትና ቀውስ የሚያባብስ ምስል ከመጠቀም ቢቆጠቡ መልካም ይሆናል።

በሶማሌና በኦሮሚያ ክልል ውሉ በወጉ በማይታወቅ ጉዳይ እንዲህ ያለው ቀውስ ተከትሏል። ህጻናት፣ እናቶችና አዛውንቶች ሰለባ ሆነዋል። ማን ነው ተጠያቂ? ምንስ ምክንያት ይቀርብለታል? መንግስት አለ በሚባልበት አገር ዜጎች መታወቂያ እየተጠየቁ ሲዘረፉና ሲባረሩ ማየት ውድቀት ነው። እንደ አገርም ተስፋ ያስቆርጣል። የሁለት ክልል ሃላፊዎችና ባለስልጣኖች በቃላት ጦርነት ሲያብዱ ማየት ያማል። ቀጣዩስ ምንድን ነው?

ቀደም ሲል አማራ በወረንጦ እየታደነ ሲፈናቀል፣ ህጻናት ከክልላችን ውጡ የሚል ደብዳቤ ሲጻፍላቸው ጠንከር ያለ ርምጃ ተወስዶ ቢሆን ኖሮ እንዲህ መረን የወጣ ደረጃ አይደርስም ነበር። ሁሌም ችግሩ ክህዝብ ፍላጎትና እምነት ያፈነገጠ የአስተዳደር ሂሳብ ነው። ዓላማው በሚታወቅ የጎሳ አስተሳሰብ አገሪቷን የበለቷት ህወሃቶች በዚህ የህዝብ እልቂትና መፈናቀል ምኑ እንደሚያረካቸው ለማንም ግልጽ አይደለም። ከስህተታቸው ለመማር አለመሞከራቸው ሲታሰብ ደግሞ ይብልጥ መጭውን ጊዜ አስፈሪ ያደርገዋል።

በተራ መፈክርና ቃላት ፍብረካ ” የኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል በምንደነቁርበት ወቅት ክዝቅታውም ወርደን የእርስ በእርስ እልቂት ውስጥ ገባን። ነገስ? አማራ ክልል እንዴት ነው? የተስፋፊነትና የድንበር ግጭት …..

ፎቶ – ማህበራዊ ገጾችና የተለያዩ ምንጮች

This slideshow requires JavaScript.

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s