ጀነራል መላኩ ኢህአዴግን ከዱ ፤ ብአዴን ናቸው

adisu

ዛጎል ዜና – በሚኒስትር ማእረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የፕሮቶኮል ሃላፊ ኢህአዴግን መክዳታቸው በተነገረ ቀናት ልዩነት ጀነራል መላኩ ሽፈራው ጥሩነህ በተመሳሳይ መጥፋታቸው ተሰማ። ከኢህአዴግ በኩል ጉዳዩን አስመልክቶ የተባለ ነገር የለም። ከአገር እንዳይወጡ የተከለከሉ ባለስልጣናትና “ልማታዊ” ባለሃብቶች እንዳሉም ቀደም ሲል ጀምሮ ሲገለጽ መቆየቱ የሚታወስ ነው።
ህወሃት ያቋቋመው ብአዴን አባል በመሆናቸው የሚታወቁት ብርጋዴር ጀነራል መላኩ፣ አሜሪካን ተካሂዶ በነበር የአይሲስ ዓለም ዓቀፍ ስብሰባ ለመሳተፍ በውጭ ጉዳይ ሚንስትር ወርቅነህ ገበየሁ ከተመራው ልዑክ አንዱ ነበሩ። ኢሳት ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳስታወቀው ጀነራሉ ወርቅነህ ገበየሁን ተለይተው ክድተዋል። በአሜሪካ ጥገኝነት ጠይቀዋል።
በመከላከያ የወታደራዊ ሰራዊት የድህንነት መምሪያ ሲያገለግሉ የነበሩት እኚሁ ከፍተኛ መኮንን ከላይ በተጠቀሰው ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ ላይ ከተገኘው የልዑካን ቡድን ተለይተው ጥገኝነት መጠየቃቸውን አስመልክቶ ከኢህአዴግ በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።
የአቶ ሃይለማሪያም ቢሮ በሌሉበት መበርበሩን፣ ቢሮው እንደተበረበረ ቢናገሩ የእሳቸውም ሆነ የአቶ ሃይለማሪያም ድህንነት አደጋ ላይ እንደሚወደቅ ” አይምሩንም ” ሲሉ የተናገርይት ባለስልጣን አቶ ባዬ በተመሳሳይ መክዳታቸው ይታወሳል።

ባዬ
ከቀናት በፊት በተመሳሳይ ለስብሰባ ወደ አሜሪካ ያቀኑት የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ፅሕፈት ቤት የፕሮቶኮል ኃላፊ / በሚኒስትር ማዕረግ/ አቶ ባዬ ታደሰ ተፈሪ በአሜሪካ ሬዲዮ ድምጻቸውን በማሰማት ሊከዱ የወሰኑት ለህይወታቸው በመፍራት እንደሆነ አረጋግጠዋል። ከዚያም በዘለለ በኢህአዴግ ውስጥ የእርስ በእርስ አለመግባባት ቀውስ ወደ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱንም አመልከተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ቁልፍም እስካሁን በጃቸው መኖሩን አረጋግጠዋል።
አቶ ባዬ በቤተመንግሥት ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ ያገለገሉት ናቸው። ዩናይትድ ስቴትስ የመጡት በ72ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ለመገኘት ጠ/ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከመሩት የኢትዮጵያ ሉዑካን ቡድን ጋር ነበር፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s