የቅማንት ድምጸ ውሳኔ በኢህአዴግ ጸደቀ፤ ሰባት ቀበሌዎች በነበሩበት ለመተዳደር ወሰኑ፤

ሰባት የቅማንት ቀበሌዎች ቀደም ሲል በነበሩበት አስተዳደር ለመቀጠል የሚያስችላቸውን ውሳኔ ማሳለፋቸውን የፌደሬሽን ምክር ቤት አረጋገጠ። አንድ ቀበሌ በቅማንት አስተዳደር ሰር ለመጠቃለል መወሰኑም ተጠቁሟል። ይህንኑ አስቀድሞ የተገለጸውን የህዝብ ድምጽ ወጤት የፌደሬሽን ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ አጽድቄያለሁ ሲል ዛሬ አስታውቋል።

የህዝበ ውሳኔውን አስፈላጊነት በመቃወም አስቀድመው የተከራከሩ ቢኖሩም ሰሚ አላገኙም ነበር። ሕዝብ ሊወስን ይገባል በሚል የድምጽ አሰጣጡ እንደተካሄደ የተሰጠውን ድምጽ ዛጎልን ጭምሮ የተለያዩ ሚዲያዎች ዘግበውት ነበር።

ይህንን ያንብቡ – በሕዝበ ውሳኔ – ሕዝብ መሰረቱ የሆነውን የአማራነት ማተቡን አተመ!!

ቢቢሲ በፌደሬሽን ምክር ቤት የህዝብ ግኑኝነት እና ኮሚኒኬሸን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ገብሩ ገ/ስላሴ ጠቅሶ እንደዘገበው ውሳኔውን የተመለከተው የፌደሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ውጤቱን በሙሉ ድምፅ አጽድቆታል።

የድምጽ አሰጣጡ በተካሄደበት እለት ውጤቱን የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ታዛቢዎችና ድምጽ ቆጣሪዎች ይፋ ቢያደርጉትም የፌደሬሽን ምክር ቤት ለጊዜው አስተያየት ለመስጥት እንደሚቆጠብ ተናግሮ እንደ ነበር ይታወሳል። አራት ቀበሌዎች ድምጽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ከውሳኔው መውጣታቸውን ይምርጫ ቦርድ ሃላፊን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።

ፎቶ ምስጋና ቢቢሲ አማርኛ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s