እናት ልጇን ተርባለች !! የእስር ጊዜውን የጨረሰው ልጅዋ አልተፈታም

“ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አይፈታም” የዝዋይ እስር ቤት

Image result for temesgen desalegn

ተመስገን የሚገኝበት የዝዋይ እስር ቤት ሀላፊዎች ሶስት ዓመት የእስር ጊዜውን ያለ አመክሮ ቢጨርስም፣ ያለ አንዳች ተለዋጭ የፍርድ ቤት ማዘዣና ምክንያት አንፈታም ማለታቸው ተሰማ። ድርጊቱ የተመስገን እስር አስቀድሞም ፖለቲካዊ መሆኑንን ያመላከተና ፍጹም አግባብነት የሌለው እንደሆነ ከየአቅጣጫው እየተዘገበ ነው።

የሶስት ዓመት የእስር ጊዜውን ያጠናቀቀው ተመስገን ከዝዋይ የመለቀቁ ዜና ሳይሆን ብዙዎችን ያጓጓው ሶስት ዓመት የማቀቁት እናቱ እረፍት የማገኘታቸው ጉዳይ ነበር። ተመስገን በታመመበትና የት እንዳለ ለጊዜው ባልታወቁባቸው ቀናቶች ” ልጄን ልቀቁልኝ ፣ ልጄ የት ነው? ልጄን … ” እያሉ ሲንሰፈሰፉ ለሰማ የተመስገን መፈታት ከዜናና ከሚዲያ ፍጆታ በላይ ለቤተሰቡ አስፈላጊ ነው።

በርካታ ሰዎች በተመሳሳይና በባሰ ሁኔታ በሚታሰሩበትና ፣ እስር ቤት ከሚማቅቁበት ስፍራ ተመስገን የእስር ጊዜውን ጨረሶ መውጣቱ ለእናቱ፣ በየቀኑ ዝዋይ ለሚመላለሱት ለቤተሰቦቹና ወዳጆቹ እረፍት ነውና የማሰሪያ ዋራንቲ የቆረጣችሁ ወገኖች እባካችሁን መመሪያ ስጡለት ወይም የሰጣችሁትን መመሪያ አንሱለት።

የተመስገን ወንድም የዝዋይ እስር ቤት እስሩን በፈጸመበት ቀነ ወንድሙ እንደማይፈታ እንዳረጋገጡለት ተናግሯል። ክልጃቸው በላይ የማቀቁት አዛውንት እንደ እርጉዝ ቀን ቆጥረው ልጃቸውን ለመሳም፣ አጣፍጠው የሰሩትን ለማጉረስ የደርሱበትን ቀን ማሳለፍ በየትኛውም መስፈርት ልክ አይሆንም። አረመኔነት ነው። ከሴት ያለመፈጠር ያህል ነው። የተመስገን እናት ሶስት ዓመት መንሰፍሰፍዎትን አምላክ ያየዋል። ከፈጣሪ ፊት የሚደበቅ አንዳችም ነገር የለም። እንባዎትን ፈጣሪዎ ያየዋል። የርስዎን ብቻ ሳይሆን በየአቅጣጫው የሚፈሰው እምባ ከሃያሉ አምላክ እይታ ውጭ አይደለምና ፈጣሪዎ ያግዝዎት፤ ልጅዎን ይገናኙ ዘንድ የዝግጅት ክፍላችን መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s