“ሦስት ዓመት ቁጥሩ ሲጠራ ቀላል ይመስላል ለጨለማ ቤት ግን ብዙ ነው” ተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ተፈቶ ከእናቱ ወ/ሮ ፋናዬ እርዳቸው ጋር ሰላምታ ሲለዋወጥ።

“ሦስት ዓመት ቁጥሩ ሲጠራ ቀላል ይመስላል ለጨለማ ቤት ግን ብዙ ነው” ብሏል። የወገብና የጆሮዬ ሕመም አብሮት እንዳለና ዝዋይ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ባቱ ሆስፒታል የተሻለ ሕክምና ያስፈልግሃል ብሎት እንደነበር ነገር ግን ያንን ማግኘት እንዳልቻለ ገልፆልናል።

በፍትሕ ጋዜጣ አዘጋጅነቱ በጻፈው ጹሑፍ ክስ ቀርቦበትና የሦስት ዓመት እስራት ተፈርዶበት በዝዋይ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዛሬው ዕለት ከእስር ተለቆ ከቤተሰቦቹ ጋር ተቀላቅሏል። ማምሻውን ጽዮን ግርማ አነጋግራዋለች።

የተፈረደበትን የሦስት ዓመት ፍርድ ያለ አመክሮ ያጠናቀቀው አርብ ዕለት የነበረ ሲሆን ቤተሰቦቹ ይፈታል ብለው የጠበቁትም በዛው ዕለት እንደነበርና የእስር ቤቱ ኃላፊዎች “አይፈታም” የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው ቤተሰቦቹ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀው ነበር።

ዛሬ ቤተሰቦቹን ስለሁኔታው ጠይቀናቸው ተመስገን ከአርብ ምሽት ጀምሮ የረሃብ አድማ አድርጎ እንደነበር ገልፀው ዛሬ ለጥየቃ ሲሄዱ ከእስር እንደተፈታ ተናግረዋል።

የተመስገንን መፈታት ተከትሎ ዓለምአቀፍ የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋች ቡድን /ሲፒጄ/ የአፍሪካ ቀንድ ተከራካሪ አንጄላ ኲንታል (Angela Quintal) በማኅበራዊ ገፃቸው የጋዜጠኛ ተመስገንን መፈታት በገለጹ በኋላ “እስክንድር ነጋን ሌሎች በጣም በርካታ ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ በእስር ላይ ይገኛሉ የኢትዮጵያ መንግሥት እነርሱንም ከእስር ሊፈታ ይገባል” ብለዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s