የአቶ በቀለ ገርባ የይግባኝ መከራከሪያ ተደመጠ

Image may contain: one or more people and people standing

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ፣ የይግባኝ መከራከሪያቸውን አቀረቡ፡፡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም አቶ በቀለ ገርባ ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አድርጎ የነበረ ሲሆን፣ እሳቸውም የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ጠይቀዋል፡፡ አቶ በቀለ ገርባ ከዚህ ቀደም የተከሰሱት በሽብር ወንጀል ሲሆን፣ ክሱ ወደመደበኛው የወንጀል ድርጊት መቀየሩን ተከትሎ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ በውጭ ሆነው እንዲከራከሩ ጠይቀው ነበር፡፡
ትላንት ጥቅምት 9 ቀን 2010 ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ በቀለ ገርባ፣ የተጠቀሰባቸው የወንጀል ዓይነት ዋስትና የማያስከለክል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዋስትና እንደከለከላቸው በመግለጽም፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔውን ሽሮ የዋስትና መብታቸውን እንዲያከብር ጠይቀዋል፡፡ ዓቃቤ ህግ አቶ በቀለ በዋስ ቢፈቱ ከሀገር ሊሸሹ ይችላሉ፣ ፍርድ ቤት ላይቀርቡ ይችላሉ የሚሉና ሌሎች ሰበቦችን በመደርደር ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸውን እንዳያከብር ተከራክሯል፡፡ የተከሳሽ ጠበቃ የሆኑት አቶ አመሃ መኮንን፣ ደንበኛው የተጠቀሰባቸው የወንጀል ዓይነት በፍጹም ዋስትና የማያስከለክል እንደሆነ በመግለጽ፣ ፍርድ ቤቱ ደንበኛቸውን በዋስ እንዲለቅ ጠይቀዋል፡፡
ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት አቶ በቀለ ገርባ ከዚህ ቀደም ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረጉ፣ ከጠበቃቸው ጋር በመማከር ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይዘውት ሔደዋል፡፡ በተከሳሽ ጠበቃ እና በዓቃቤ ህግ መካከል ያለውን የዋስትና መብት የተመለከተ ክርክር ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 20 ቀን 2010 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ አቶ በቀለ ገርባ በእነ ደጀኔ ጣፋ የክስ መዝገብ ከተከሰሱ የኦፌኮ ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ የኦፌኮ አመራሮች ከሊቀ መንበሩ ዶ/ር መረራ ጉዲና ጀምሮ በጠቅላላው እስር ቤት እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

BBN news 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s