በቀለ ገርባ በዋስ ለመለቀቅ ባቀረቡት ይግባኝ አሸነፉ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አንደኛ ሰሚ ይግባኝ ሰሚ ወንጀል ችሎት ባቀረቡት ይግባኝ በጠየቁት መሰረት በ30ሽህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ተወሰነላቸው። አቶ በቀለ በሽብር ወንጀል ቢከሰሱም ከሳሽ አቃቤ ህግ በቂ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ ያለ ፍርድ ለዓመታት መታሰራቸው ከየአቅጣጫው ትችትና ተቃውሞ ሲሰነዘር መቆየቱ ይታወሳል።

አቶ በቀለን ጨምሮ ዶክተር መረራ ጉዲና እና የተለያዩ የፓርቲ ሃላፊነት ያላቸው፣ የኦሮሞ ልጆች እንዲፈቱ በሰላማዊ ሰልፍና በተለያዩ ተቃውሞዎች በከፍተኛ ደረጃ ሲጠየቅ እንደነበርም ይታወሳል። ዚናውን ይፋ ያደረገው ፋና የሚከተለውን ዘግቧል።

በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሽብር ወንጀል ተከሰው የነበሩት የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ዋስትና ተፈቀደላቸው። በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸው ሲታይ የነበረው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ባቀረቡት የዋስትና የይግባኝ ጥያቄ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተቀብሎ አፅድቆታል።

አቶ በቀለ ገርባ በዚሁ ችሎት የመከላከያ ምስክር ለማሰማት በቀጠሮ ላይ ያሉ ሲሆን፥ በተደጋጋሚ ባቀረቡት ይግባኝ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ በመደረጉ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አንደኛ ይግባኝ ሰሚ ወንጀል ችሎት ይግባኝ ብለው ነበር። ይህንን የይግባኝ ጥያቄያቸውን የመረመረው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ አዟል። ነገር ግን የመከላከያ ምስክር የማሰማት ሂደቱ የሚታይ ይሆናል ተብሏል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s