በኤርትራ አስመራ ከተማ ዛሬ በድንገት በተደረገ የተቃውሞ ስልፍ ተማሪዎችና ፖሊሶች ተጋጩ።

ዋዜማ ራዲዮ- የትምህርት ቤታቸው የቦርድ ዳይሬክተር መታሰራቸውን የተቃወሙ ተማሪዎች በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቢሮ ዳጃፍ ስልፍ ለማድረግ ሲሞክሩ በታጣቂዎች የተኩስ እሩምታ ገጥሟቸዋል።

በግጭቱ ስለደረሰው ጉዳት የታወቀ ነገር የለም። በኤርትራ ይህን መስል ስልፍ ማድረግ ፈፅሞ የማይታስብ ሆኖ ቆይቷል። የቦርድ ስብሳቢው ሀጂ ሙሳ የታሰሩት በታሪኩ ከእስልምና እምነት ጋር የተያያዘው ትምህርት ቤት ሴት ተማሪዎች ሂጃብ እንዲያወልቁ በመንግስት የተሰጠውን ትዕዛዝ ባለመቀበላቸው ነበር። ትምህርት ቤቱ ከሀምሳ አመት በፊት የተቋቋመ ነው።ማክስኞ በተደረገው ስልፍ ላይ ከተማሪዎቹ በተጨማሪ የእስልምና ተከታይ የሆኑ የአስመራ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
ሀጂ ሙሳ የዘጠና አመት አዛውንት ሲሆኑ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያላቸው ናቸው።
በአስመራ የፀጥታ ሀይሎች ምሽቱን ቤት ለቤት በመዞር ቁጥራቸው ያልታወቀ ስዎችን ያሰሩ ሲሆን አንዳድንድ ወጣቶች ከተማዋን ጥለው ሸሽተዋል።
በአሰመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የፀጥታ ማሳሰቢያ ያወጣ ሲሆን በመሀል አስመራ በተለያዩ አቅጣጫዎች የተኩስ እሩምታ መሰማቱን ተናግሯል።  ከኤርትራ መንግስት የተሰጠ አስተያየት የለም።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s