በቀለ ገርባ እንዲፈቱ የተላለፈው ውሳኔ ታገደ

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ይግባኝ መጠየቁን በመጠቀስ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ አጣሪ ችሎት ለአቶ በቀለ ገርባ የተፈቀደውን ዋስትና ማገዱን የኢህአዴግ ሚዲያዎች ዘገቡ። ሚዲያዎቹ እንዳሉት ጉዳይ ለሰበር ችሎት ያስቀርባል ተብሏል።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ አንደኛ የወንጀል ችሎት አቶ በቀለ ገርባ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። አቶ በቀለ የዋስትና መብታቸው ሊከበር እንደሚገባ ጠቅሰው በጠየቁት ይግባኝ መሰረት እንዲፈቱ መወሰኑንን ተከትሎ፣ ልጃቸው በአባቷ መፈታት የተሰማትን ስሜት ገልጻ ነገር ግን አባቷ አለመፈታታቸው ስጋት ላይ እንደጣላት አስታውቃ ነበር።

ሚዲያዎቹ እንዳስታወቁት ጉዳዩ በሰበር ሰሚ አጣሪ እንዲታይ ከመወሰኑ በቀር መቼ እንደተቀጠረ ይፋ አላደረጉም። በትልሉ ግን በሰበር ሰሚ አጣሪ ችሎት ይህ ውሳኔው ታግዷል። አቶ በቀለ ገርባም መልስ እንዲሰጡ መታዘዛቸው ተመልክቷል።

Advertisements

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.