“የሼህ መሐመድ እስር አልተረጋገጠም”በፌስ ቡክ ገጻቸው – ” ሼህ አልአሙዲ አልታሠሩም!” – ” መታሰራቸው ተረጋግጧል”ሚዲያዎች

ሺህ መሐመድ አል አሙዲ መታሰራቸው አለመረጋገጡን  Honorable Dr Sheik Mohammed Hussien Ali Al-Amoudi በተሰኘው የፌስ ቡክ ገጽ ላይ ተገልጿል። ገጹ በሙስና ተጠርጥረው ከታሰሩት ዝርዝር ውስጥ ስማቸው አለመጠቀሱን፣ ይሁን እንጂ “businessman” በሚል ባቻ መጠቀሳቸውን ያወሳል። ገጹ ” አልተረጋገጠም” በሚል ከመዘገቡ ውጪ አላስተባበለም። እንዲህ ይነበባል። ገጹ መረጃውን ከዘከሪያ መሐመድ ገጽ መገኘቱንም አስታውቋል።

 

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ልዑላንን ጨምሮ በሥራ ላይ ያሉና የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን፣ እንዲሁም ታዋቂ ቱጃሮችን በሙስና ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ተሰማ፡፡ በቁጥጥር ስር በዋሉት ቱጃሮች ውስጥ መሐመድ አል አሙዲ የተባሉ ‹‹ቢዝነስማን›› እንደሚገኙበት የኒ ሸፈቅ የተሰኘ ድረ ገጽ ጽፏል፡፡ ድረ ገፁ በቱጃሮች ዝርዝር ውስጥ መሐመድ አል አሙዲ “businessman” መሆናቸውን ከመጥቀሱ በቀር፣ ተጨማሪ መረጃ አልሰጠም፡፡ የተጠቀሱት ግለሰብ በእናታቸው ኢትዮጵያዊ የሆኑት መሐመድ ሑሴን አል አሙዲ ይሁኑ ወይም ሌላ ስመ ሞክሼ ለጊዜው በእርግጠኛነት መናገር አንችልም፡፡ ( ይህ ዜና ከዘካሪያ መሐመድ ገጵ የተገኘ ነው።)

የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ፍሬው አበበ በፌስ ቡክ ገጹ ሼኹ አለመታሰራቸውን እንዲህ ሲል አስፍሯል። ” የእሳቸው ሁኔታ ላስጨነቃችሁ ወገኖች ምሥጋናችን የላቀ ነው ሲል አመልክቷል።

ሼህ አልአሙዲ አልታሠሩም!Image may contain: one or more people

የክብር ዶክተር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ በተለይ በማህበራዊ ድረገጶች ሳዑዲ ውስጥ እንደታሰሩ ተደርጎ እየተዘገበ ያለው ስህተት ነው። ሼህ ሙሐመድ በአሁን ሰዓት በመደበኛ ሥራቸው ላይ መሆናቸውን ቅርበት ካላቸው ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል። የእሳቸው ሁኔታ ላስጨነቃችሁ ወገኖች ምሥጋናችን የላቀ ነው።

ዘ ኒው ዮርክ ታይም የሼኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸውን ይፋ አድርጓል። ይህ ዜና እስከተጠናከረ ድረስ ታይም ማስተባበያ አልሰጠም። የጅርመን ሬዲዮና ቪኦኤ አማርኛ ሁለቱም ዜናውን ታዋቂና ታማኝ የዜና አውታሮችን ዋቢ አድርገው ዜናውን አውጀዋል።

ስለሺ ሽብሩ ከሪያድ ተጨማሪ ማስረጃ ማሰባሰቡን በመግለጽ የእሳችውን እስር ማረጋገጡን አመልክቷል። እርምጃው አጣዳፊ፣ በቂ ዝግጅት የተደረገበት፣ በባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ታሰሩ ቢባልም ስለሺ ሁሉም ለየብቻ መታሰራቸውን አመልክቷል። ከላይ ያለውን አስፈንጣሪ በመጫን ስለሺን ያድምጡ። ከታሳሪዎቹ መካከል የኦሳም ቢላደን ወንድም ይገኙበታል።

ፎቶ የተወሰደው በስማቸው ከተሰየመው የፌስ ቡክ ገጽ ነው

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s