በአማራ ክልል ሃሰተኛ የገንዘብ ኖቶችና ማስረጃዎች ያዘጋጃሉ የተባሉ ተያዙ

 በአማራ ክልል ሀሰተኛ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የገንዘብ ኖቶችንና ሌሎች የትምህርት ማስረጃዎችን ያዘጋጃሉ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ተይዘው ለህግ ቀረቡ።

የክልሉ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሠረት ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እንዲታይ እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

ግለሰቦቹ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ፣ የብቃት ምዘና፣ የስራ ልምድ፣ መንጃ ፈቃድና ሌሎች ሀሰተኛ ሰነዶችን በማተም የወንጀል ስራ ሲያከናውኑ እንደነበርም ተገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሲውሉ ተዘጋጅተው ያልተሰራጩ 620 ሃሰተኛ ባለመቶና አራት ባለ ሃምሳ የብር ኖት፣ 162 ሀሰተኛ ባለመቶ የአሜሪካ ዶላርና መሰል የገንዘብ ኖቶች መያዛቸውን የኮሚሽኑ የምርመራና አቃቢ ህግ ዳይሬክተር አቶ ተመስገን መላክ አስረድተዋል።

የሳዑዲ ሪያልና የህንድ ሩፒ የገንዘብ ኖቶች እንዲሁም በሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ያልተሰጡ የ10ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናና የመሰናዶ ትምህርት ማጠናቀቂያ ውጤቶችን በመቀያየር የተሰሩ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችም ተይዘዋል።

በተለያዩ የግልና የመንግስት ኮሌጆች ስም የተዘጋጁ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች፣ መንጃ ፈቃዶችና የጤና ሙያ ፈቃዶች መያዛቸውንም ጠቁመዋል።

ግለሰቦቹ ለወንጀል መስሪያነት ሲገለገሉባቸው የነበሩ ላፕቶፕ፣ ዴስክቶፕ፣ ሁለት ባለከለር ፕሪንተሮች፣ አንድ ከለር አልባ ፕሪንተር፣ ፍላሾች እንዲሁም የተለያዩ የማህተም አርማዎችና ሌሎች ቁሳቁሶችም ተይዘዋል ነው ያሉት። 

ከዚህ ጋር ተያይዞም ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ፣ መንጃ ፈቃድና መታወቂያ ለመስራት ተጠርጣሪዎቹ የተቀበሏቸው የ48 ሰዎች ጉርድ ፎቶግራፎችም ተገኝተዋል።

ኮሚሽኑም በተጠርጣሪዎች ላይ ሲያደርግ የቆየውን ምርመራ አጠናቆ የሰነድ ማስረጃዎችን ወደ አቃቢ ህግ መርቶ ክሱን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቅረቡን የኢዜአ ዘገባ ያስረዳል።

(ኤፍ ቢ ሲ)

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s