3 ነጥብ 2 ሚልየን ብር አራጣ በማበደር የተከሰሱት ባልና ሚስት ጥፋተኛ ተባሉ

13 በመቶ ወለድ በማስከፈል 3 ነጥብ 2 ሚልየን ብር በአራጣ በማበደር የተከሰሱት ባለትዳሮች ጥፋተኛ ተባሉ። ተከሳሾቹ ትግሉ ሀይሌና ባለቤቱ ጌጤነሽ ሀይለሚካኤል ይባላሉ። የአቃቤ ህግ ክስ ተከሳሾቹ አቶ ደስታ ተሾመ ለተባለ የግል ተበዳይ ከቻይና ያስመጣቸውን እቃዎች ለባንክ ሰነድና የጉምሩክ ቀረጥ ከፍያ ለመፈጸም ባለመቻሉ 3 ነጥብ 2 ሚልየን ብር በአራጣ አበደረውታል።

የክስ ዝርዝሩ እንደሚያስረዳው የግል ተበዳይ ደስታ ተሾመን ሁለት ባለ3 ሚልየን ብር ቼክ በማስፈረምና 13 በመቶ ወለድ እንዲከፈል በማድረግ በወር 421 ሺህ 720 ብር እንዲከፍልም አስገድደውታል ነው ያለው አቃቤ ህግ በክሱ። ግለሰቡም ወለዱን መክፈል ባለመቻሉ ለሀግ አቤት ብሏል።

ከሳሽ አቃቤ ህግም በግለሰቦቹ ላይ በአራጣ ማበደር ወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል። ለተከሳሾቹ ክሱ ደርሷቸው ተነቦላቸው እንዲረዱት ከተደረገ በኋላም በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል የወንጀል ድርጊቱን አልፈጸምንም በማለት ክደው ተከራክረዋል። ነገር ግን በአቃቤ ህግ ያቀረበባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ማሰተባበል ባለመቻላቸው የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛው የወንጀል ችሎት ጥፋተኛ ብሏቸዋል። በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ በተከሳሾቹ ላይ የቅጣት ውሳኔ ለማሳለፍ ለህዳር 13 ቀን 2010 ዓ ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

FBC – በሰለሞን ጥበበስላሴ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s