የመረጃ ጠላፊዎች ከኤ.ቲ.ኤም ማሽኖች ከ10 ሚሊየን ዶላር ያላነሰ ገንዘብ ዘርፈዋል

የሩሲያ ቋንቋ የሚናገሩ የመረጃ ጠላፊዎች የኤ ቲ ኤም ማሽኖችን በመጥለፍ በአሜሪካ፣ ብሪታኒያ እና ሩሲያ ከሚገኙ 20 ኩባንያዎች ከ10 ሚሊየን ዶላር ያላነሰ ገንዘብ መዝረፋቸው ተነግሯል።

ገንዘብ ዘራፊ የመረጃ ጠላፊዎቹ አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ማውጣት የሚጠበቅበትን የገንዘብ ልክ የሚገድበውን ስርዓት በማጥፋት ነው ገንዘቡን የወሰዱት ተብሏል።

ከዚህም ባሻገር ገንዘብ ዘራፊ የመረጃ ጠላፊዎቹ በዩናይትድ ስቴትስ እና በደቡብ አሜሪካ የሚገኙ ከ200 በላይ ባንኮች የሚጠቀሙባቸውን የቴክኖሎጂ ሰነዶች ጠልፈዋል።

እነዚህ ቴክኖሎጂ ሰነዶች በቀጣይ ጊዜ የመረጃ መረብ ጥቃት ለማድረስ ሊጠቀሙባቸው እንደሚችል ነው የተጠቆመው።ግሮፕ-አይቢ (Group-IB) የተባለው የመረጃ መረብ ደህንነት ላይ የሚሰራ ኩባንያ ከአውሮፓ ማዕከላዊ ፖሊስ (ዩሮፖል) እና ከሩሲያ መንግስት ጋር በመሆን የሳይበር ጥቃት ወንጀሉን እየመረመርኩ ነው ብሏል።

ገንዘብ ወሳጆቹ (MoneyTaker) የሚባሉት እነዚህ የሳይበር ጥቃት ወንጀለኞች ከፈረንጆቹ 2016 ጀምሮ በአሜሪካ ኩባንያዎች ባደረሷቸው 16 ጥቃቶች በእያንዳንዳቸው በአማካይ 500 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መውሰዳቸው ነው የተነገረው።በሩሲያ ባንኮች ላይ ደግሞ ሶስት ጊዜ ጥቃት ያደረሱ ሲሆን፥ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ዘርፈዋል።

በ2016 ታህሳስ ወር ደግሞ መቀመጫቸውን በብሪታኒያ ባደረጉ የሶፍትዌር አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት አድርሰዋል። የብሪታኒያ የፋይናንስ ተቋማት ስለወንጀሉ ያሉት ነገር የለም።

fana

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s