ጣሊያናዊው ‘የሞት አምቡላንስ’ ሠራተኛ – በአስከሬን 360 ዩሮ ኮሚሽን ለማግኘት በመርፌ ሰዎችን መግደሉ ተደርሶበት ተያዘ

Image copyrightGETTY IMAGES

በጣሊያኗ ደሴት ሲሲሊ የሚኖር የአምቡላንስ ሰራተኛ ከቀብር ማስፈፀም ገንዘብ ለማግኘት ሲል ህሙማንን ይገላል በሚል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። ግለሰቡ ሦስት ፅኑ ህሙማንን ወደቤታቸው እያደረሳቸው እያለ መርፌ ወግቶ በመግደል ነው የተጠረጠረው።

ለእያንዳንዱ አስክሬን 300 ዮሮ (265 ፓውንድ) ክፍያ ተቀብሏልም ተብሏል። የጣልያን መገናኛ ብዙሃን የዚህ ‘የሞት አምቡላንስ’ የወንጀል ዜናን ሲቀባበሉት ነበር።

ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለው ተጠርጣሪ ግለሰብ የቀድሞ የማፊያ ቡድን አባል የነበረ መሆኑን የገለፀ ሲሆን፤ ለካታኒያ ከተማ ባለስልጣናት እና የምርመራ ዘገባ ለሚሰራ የቴሌቪዥን ፕሮግራም መረጃ ሰጥቷል። የአምቡላንሱ ሰራተኛ ሆን ብሎ ነፍስ በማጥፋት ወንጀል ተከሷል። ተጠራጥሪው ህሙማኑን ወደ ሚኖሩበት ቢያንካቪላ ይዟቸው ሲሄድ በወጋቸው መርፌ ምክንያት በደም መርጋት እንዲሞቱ እንዳደረጋቸው ተጠርጥሯል።

የ42 ዓመቱ ሰራተኛ በሐዘን ላይ ያሉ ቤተሰቦችን ከሲሲሊ የማፊያ ቡድን ጋር ግንኙነት ላለው የቀብር አስፈፃሚ በመጠቆም ኮሚሽን እንደሚቀበል ታውቋል። ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ይህ ተግባር ከ2012 ጀምሮ እየተፈፀመ እንደሆነ እና ሌሎች ተበዳዮችም ሊኖሩ እንደሚችሉ ነው።

ምርመራውን እያደረጉ ያሉ አካላት እንዳሉት በቢያንካቪላ በርካታ ሞቶች እየተመዘገቡ ሲሆን እስካሁን ግን 12 ብቻ ሊመለከቷቸው የሚገቡ ጉዳዮች እንደገጠሟቸው እና ሌሎች ሦስት ደግሞ ለክስ እንደቀረቡ ተናግረዋል።

ቢቢሲ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s