የተከሳሾች ጠበቃ – እነ ለማ መገርሳ ፍርድ ቤት ቀርበው እንደሚመሰክሩ ገልጸውልኛል

በእነ ጉርሜሳ አያኖ የክስ መዝገብ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተከሳሾች በመከላከያ ምስክርነት የተጠቀሱት አቶ ለማ መገርሳ፣ ዶ/ር አብይ አህመድ፣ ወ/ሮ ጫልቱ ሰኒ እና አቶ አባዱላ ገመዳ ነገ ታህሳስ 19/2010 ዓም ፍርድ ቤት ቀርበው መመስከር እንደሚችሉ መግለፃቸው ተሰማ። ዘወትር የፍርድ ቤት ውሎ እግር ለእግር እየተከታተለ የሚዘግበውና መረጃ የሚያጋራው ጌታቸው ሽፈራው ይህንን ያረጋገጠው ከተከሳሾች ጠበቃ ነው።

ከ1ኛ እስከ 4ኛ ያሉት ተከሳሾች ጠበቃ አቶ አብዱልጀባር ሁሴን ባለስልጣናቱን በአካል አግኝተው እንዳነጋገሯቸው ዛሬ ታህሳስ 18/2010 ዓም ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት አስረድተዋል። ባለስልጣናቱ በሁለቱ ቀን ቀጠሮ በስብሰባ ምክንያት መቅረብ እንዳልቻሉ፣ ለነገ ታህሳስ 19/2010 ዓም ቀርበው ሊመሰክሩ እንደሚችሉ እንደገለጹላቸው ጠበቃው ለችሎቱ አመልክተዋል።

በሌላ በኩል የ4ኛ ተከሳሽ በቀለ ገርባ የመከላከያ ምስክር የሆኑት አቶ አንዱዓለም አራጌ ዛሬም ያልቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥብቅ ትዛዝ እንዲሰጥ ጠበቃ አብዱልጀባር ጠይቀዋል።

አቶ ሃይለማሪያም በስራ ብዛት መመስከር እንደማይችሉ ጠቅሰው በጽፈት ቤታቸው አማካይነት ምላሽ መስጠታቸውና አቶ በቀለ ገርባ በፖሊስ ታስረው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤት እንዲያዝ መጠየቃቸው በተመሳሳይ መዘገቡ ይታወሳል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s