Advertisements

ኬንያ ሺሻ ሙሉ በመሉ ጥቅም ላይ እንዳይውል አገደች

ኬንያ ከታኅሳስ 19/2010 ዓ.ም ጀምሮ ሺሻ ማስመጣት፣ መሸጥም ሆነ መጠቀም የሚከለክል ሕግ አወጣች። የኬንያ ጤና ሚንስትር ክሌዎፓ ማይሉ በትላንታው ዕለት እንዳስታወቁት ሺሻ ሲጠቀሙም ሆነ አስመጥተው ሲሸጡ የተያዙ ግለሰቦች 50 ሺህ የኬንያ ሽልንግና (500 ዶላር) ከ6 ወር በማያንስ እሥራት ይቀጣሉ።

ኬንያ ሺሻን በማገድ ከታንዛኒያና ከሩዋንዳ ቀጥላ ሦስተኛዋ ሃገር ሆናለች። “ሸሻን ማገድ ያስፈለገን ከሚያደርሰው የጤና እክል እና ማሕበራዊ ቀውስ አንፃር ነው” ሲል የኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መግለጫ ያትታል።

ሺሻ በኬንያ በርካታ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን ከውሳኔው በኋላ ኬንያውያን ወደ ትዊተር በማምራት በእገዳው ዙሪያ ሲወያዩ ነበር። የዓለም የጤና ድርጅት በቅርቡ ሺሻ ማጨስ ጤናን እንደሚጎዳ የሚጠቁም ጥናት ማውጣቱ ይታወሳል። ፓኪስታን፣ ዮርዳኖስ፣ ሲንጋፖርና ሳዑዲ አረቢያ ሌሎች ሺሻን ያገዱ ሃገራት ናቸው።

BBC Amharic

Advertisements

Zaggolenews. የዛጎል ዜና

Editor of zaggolenews.com contact editor - zaggolenews2016@gmail.com

You may also like...

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: