ኢትዮጵያና ሶማሌላንድ የኢኮኖሚ ትስስራቸውን ለማጠናከር ተጨማሪ ወደቦችን በጋራ ለማልማት ተስማሙ፤

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ብሂ አብዲ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ በሰላምና ፀጥታ፣ በኢኮኖሚ፣ በንግድ እና ትምህርት ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማምተዋል።

ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን በመጠቀም ከግዛቲቱ ጋር ያላትን የኢኮኖሚ ትስስር እንደምታጠናክር የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም፥ ለዚህ ደግሞ የወደቡን መዳረሻ መንገድ የማልማት ስራ እንደምትሰራ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የጎረቤት አገሮችን ልማት እንደራሷ ልማት የምታይ መሆኑን ገልጸው፥ “ለሶማሌላንድ ወጣቶች የትምህርት ዕድል በመስጠት የጀመረችውን ትብብር ታጠናክራለች” ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ ኢትዮጵያና ሶማሌላንድ ተጨማሪ ወደቦችን በማልማት የኢኮኖሚ ትስስራቸውን የበለጠ ለማጠናከር መስማማታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በሶማሌላንድ አስተዳደር በተደጋጋሚ ጥቃት በመፈጸም በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት የሚያደርሰውን አልሸባብን በጋራ ለመዋጋት ኢትዮጵያ ድጋፍ የምታደርግ መሆኑንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስታወቁት።

ሶማሌላንድ ያነሳቻቸው የፖለቲካ ጥያቄዎች በኢጋድና በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ መስተናገድ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይም መወያየታቸውን አቶ ኃይለማርያም ተናግረዋል።

ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲሆን የጋራ ኮሚሽን አቋቁመው ለመስራት መስማማታቸውን ተገልጿል።

ፕሬዚዳንት ሙሴ ብሂ አብዲ በበኩላቸው ሁለቱ አገሮች ያላቸውን መልካም ግንኙነት በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ መስኮች የበለጠ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው ነው የገለፁት።
በተለይም በፀጥታ እና በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል ሲል መረጃው ያደረሰን

ኢዜአ 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s