ቆቦ ህዝብና ሰራዊት እየተታኮሱ ነው፤ የሰው ህይወት አልፏል፤ ሃይለማሪያም የት ናቸው?

በቆቦ በሰራዊቱና በሕብ መካከል የከረረ ግጭት መከሰቱ ተሰማ። ግጭቱን “ጦርነት” ሲሉ የጠሩት ክፍሎች እንደሚሉት በመዘጋጃ ቤት፣ በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ጉዳት መደረሱ ተጠቁሟል። በቀውሱ ሰዎች ሞተዋል። ጉዳዩን አስመልክቶ ከመንግስት በኩል የተባለ ነገር የለም።


በወልደያ የደረሰውን ግድያ ተከትሎ የተቀሰቀሰው የቆቦ አመጽ ወደ ጠመንጃ ልውውጥ መቀየሩን በስልክ ለኢሳት ከተናገሩ የአይን እማኝ ነው የተሰማው። እንደ አይን ምስክሩ መዘጋጃ ቤት፣ አራት ቀበሌ ጽ/ቢተ፣ፍርድ ቤት፣ ገቢዎች ቢሮ፣ ንግድ ቤቶች፣ ህንጻና የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል። እኚሁ ሰው እንዳሉት እሳቸው እስከሚያውቁት ሰባት የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል። አንድ የአጋዚ ወታደር ህይወት አልፏል።
የአካባቢው ነዋሪዎችን የጠቀሱ የማህበራዊ ገጽ አምደኛ በበኩላቸው ሁኔታው ፈር እንዳይለቅና ግጭቱ እንዳይሰፋ መስጋታቸውን ገልጸዋል። አሁን አገሪቱ የጋባችበት ቀውስና በየዕለቱ የሚሰማው ዜና የረበሻቸው ዜጎች ሁሉንም ያካተተ እርቅ ሊደረግ እንደሚገባ እየወተወቱ ነው። ኢህአዴግ በበኩሉ አገር ውስጥ ካሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር እየተደራደረ መሆኑንን እየገለጸ ነው።
አሁን እየተካሄደ ያለው ድርድር በሕዝብ ዘንድ ታማኝነትና ድጋፍ የሌላቸው እድር መሰለ የፖለቲካ ድርጅቶች በመሆኑ ውጤት እንደማያመጣ በስፋት አስተያየትና ትችት የሚሰማበት ጉዳይ ነው። በቅርብ ከእስር የተለቀቁት ጉምቱ ፓኦለቲከኛና መምህር ዶክተር መረራ ጉዲና “ሰፊ የህዝብ ድጋፍ ካላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር እውነተኛ ድርድር ይደረግ” ሲሉ በተፈቱበት ቅጽበት መናገራቸውን ፋና መጥቀሱ አይዘነጋም። ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ ከኢህአዴግ በኩል የተባለ ነገር የለም። በቆቦ ተጨማሪ ወታደሮች መላካቸውና ሄሊኮፕተር ከአየር ላይ በመሆን ለማስፈራራት መተኮሱ ተሰምቷል።

ከወልደያው ግድያ ጀመሮ የመከላከያው ” የበላይ” የሚባሉት አቶ ሃይለማሪያም ያሉት ነገር የለም። የትስ ናቸው?

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s