መረራ አምቦ ላይ ዳግም ተወለደ -የሕዝብ ፍቅር ሲፈስ መሸከም ያቅታል!!

ጉሊት ይመስል የችርቻሮ መደብር ከሸፈነው ውቡ ኢትዮጵያ ሆቴል ፊት ለፊት ቆሜ የማየውን ማመን አቃተኝ። ሕዝብ ይተማል። ሕዝብ ሁሉቃን እንደ ደራሽ ይፈስበታል። በሁሉቃ ደረት ሕዝብ ማዕበል ሆኖ ይጎርፋል። ከታቸ ከሰንቀሌ መስመር ጅምሮው በሁልም አቅጣጫ ህዝብ ይተማል። መናኸሪያ ሰው ይተራመሳል። እግሮች ሁሉ ወደ ካምቦሎጆ ያመራሉ። እዛ አንድ ድንቅ ሰው አለ። ድፍን የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚወደው ሊቅና የህዝብ ልጅ መረራ!! የጉዲና ልጅ!

አምቦ በታሪኳ ዛሬ ሙሽራዋን አከበርች። አምቦ ዛሬ ልጇን አወደሰች። መረራ የሚሆነውን ማመን አቃተው። ሕዝብ ሲወድ እንዲህ ነው። ሕዝብ ሲወድ ልቡም ይሰግዳል። አምቦ ካምቦሎጆ ጠጠር መጣያ የለም ነበር። መራራ ይህንን እንኳን አየህ። እንኳን በህይወት ኖረህ አንተው የገነባኸውን፣ ያነጽከውን፣ የተከልከውን ጽድቆልህ አየህ።
መረራ የኢትዮጵያን ሕዝብ አክባሪ፣ ለሁሉም ህዝብ እኩልነት የምትተጋ፣ ለጀግንነቱ ብሄር የሌለው፣ የኦሮሞ ልጅ፣ የአገር ኩራት እንኳን ትፈታ ዘንድ ደማቸውን በከፈሉልህ ጀግኖች መካከል ቆምክ። አምቦ እትብትህ አለበት ከተማ ብትቆምም አገር በሙሉ ትእይነቱን አይቶ ቆሞልሃል። መሪ ነህ። በህዝብ አቆጣጠርና ልብ አንተ ዋርካ ሆነህ እንደትመራ ተቀብተሃል።
እነዚህ ማሰቢያቸው የተበላሸ ሰዎች ያሰሩትና ፍልሚያ የገቡት ይህንን ሁሉ ሰው አስረው እንደሆነ ዛሬም ይገባቸው ይሆን? ሌሎች ፖለቲከኞችስ ይህንን ትረዱ ይሆን? የማይልከሰከስ ጽኑ አቋም እንዲህ ያስከብራል። ከመረራ ተማሩ!! ድጋፍ ሳይኖራቹህ በሚዲያ የምታላዝኑ ጉዳዩን ለሕዝብ ልጆች ተዉት።

mera 4

 

Image may contain: 1 person, smiling, closeup

Image may contain: 1 person, riding on a horse, horse, hat and outdoor

Image may contain: one or more people, motorcycle and outdoor

mera 4merra ambo 2

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s