አትሌቶችን ከሶስት ሚሊዮን ብር በላይ ያጭበረበረው ማኔጀር ተቀጣ፤ መሰለች መልካሙ 2.5 ሚሊዮን የሚጠጋ ብር ተዘርፋለች

አትሌት መሰለች መልካሙን ጨምሮ አምስት አትሌቶችን ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ደረቅ ቼክ በመጻፍ በማታለል ወንጀል የተከሰሰው የአትሌቶች ማናጀር ወላይ አማረ በፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ።


የቅጣት ውሳኔውን የፌደራሉ ካፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ነው ያሳለፈው። የጠቅላይ አቃቤ ህግ ክስ እንደሚያመላክተው ተከሳሽ ወላይ አማረ ወንጀሉን የፈፀመው ከ2008 እስከ 2009 ዓ.ም ባለው ጊዜ ነው።
ግለሰቡ ከአምስቱ አትሌቶች በተለያዩ ጊዜና ሀገራት ባደረጉት ውድድር የተሳትፎ የኮንትራት ውል ክፍያን ገንዘብ ሳይኖረው በአዋሽና በሌሎች ባንኮች ሂሳቡ ውስጥ ገንዘብ እንደሌለው እያወቀ ደረቅ ቼክ በመጻፍ ማታለሉ በክሱ ተጠቅሷል።
በዚህም መልኩ ለአትሌት አፀደ ፀጋዬ ከ1 ሚሊየን 15 ሸህ ብር በላይ፣ ለአትሌት መሰለች መልካሙ ከ2 ሚሊየን 368 ሺህ ብር በላይ እንምዲሁም ለአትሌት በላቸው አለማየሁ 230 ሺህ ብር እና ለሌሎችም አትሌቶች ተመሳሳይ የገንዘብ መጠን ደረቅ ቼክ በመጻፍ የማታለል ተግባር መፈጸሙ በክሱ ተዘርዝሯል።
ተከሳሹ የአትሌቶች ማናጀር ወላይ አማረ በተከሰሰበት ማታለል ወንጀል ፍርድ ቤት ቀርቦ ክሱን መከላከል ባለመቻሉ ጥፋተኛ ተብሏል።
የፌደራሉ ካፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ ወላይ አማረ በ10 ዓመት ከ11 ወራት ፅኑ እስራትና በ2 ሺህ 500 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።
በታሪክ አዱኛ – ፋና

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s