ሕዝብ ታሳሪዎችን እያስፈታ ነው፤ እነ እስክንድር ዛሬ ነጻ ይወጣሉ

እን እስክንድር ነጋንና አስዱ ዓለም አራጌን ጨምሮ  746 እስረኞች መፈታታቸውን የኢህአዴግ ሚዲያዎች ይፍ አድርገዋል። ሚዲያዎቹ አቅቤ ህግን ጠቅሰው እንዳሉት እስረኞቹ ክሳቸው ተቋርጦ ዛሬ እንደሚፈቱ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። እነ እስክንድር ስለመፈታታቸው እንጂ ይቅርታ ስለመጠየቃቸው ሚዲያዎቹ ያሉት ነገር የለም።

bekele gerba 1

አቶ በቀለ ገርባ፣ ጉርሜሳ አያና፣ አዲሱ ቡላላ፣ ደጀኔ ጣፋ፣ ጌቱ ጋሩማ፣ ተስፋዬ ሊበን እና በየነ ሩዳ በትላንትናው እለት ከእስር መለቀቃቸውን ይታወሳል። አቶ በቀለንና ሌሎችን እስረኞች  በኦሮሚያ ቲቪ ” ቂሮን፣ ሕዝብን እናመሰግናለን። የቀሩት ከተፈቱት ጋር ሲነጻጸር እስር ቤት ያሉት ቁጥራቸው …. እናም ሁሉም ሊፈቱ ይገባል” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። 

ከዩኒዘርስቲ የታፈሱ፣ የመከላከያ አባላት የሆኑ፣ ከአማራ ክልል የተጋዙ… እጅግ ሰፊ ቁጥር ያላቸው እስረኞች በማጎሪያ ቤቶች እንደሚገኙ በተደጋጋሚ መገለጹ የሚታወስ ነው። ዶክተር መረራም ከእስር ሲወጡ ራሳቸውን መንከባከብ የማይችሉ እስረኞች እንዳሉና እነዚህ ሰዎች ቀሪ ጊዜያቸውን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ቢያሳልፉስ ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

ፋና የኢህአዴግ ውሳኔ መሆኑንን ጠቅሶ ቢዘግብም፣ አብዛኛው የማህበራዊ ገጾች “ሕዝብ አሸነፈ” ሲሉ ተደምጠዋል። የፋና ዜና እንሆ፤

እስክንድር ነጋና አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ 746 ታራሚዎችና ተጠርጣሪዎች ክሳቸው ተቋረጦ ዛሬ እንደሚለቀቁ የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ገለጸ።

በአገሪቱ ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ጉርሜሳ አያና፣ አቶ አዲሱ ቡላላ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ ጌቱ ጋሩማ፣ አቶ ተስፋዬ ሊበን እና አቶ በየነ ሩዳ ክሳቸው ተቋርጦ ዛሬ ተለቀዋል።

ታራሚዎቹ እና ተጠርጣሪዎች ክሳቸው ተቋርጦ እንዲለቀቁ የተደረገው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ጉዳያቸው ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት እየታየ እንዲለቀቁ በወሰነው መሰረት ነው።

ይቅርታ የሚደረግላቸው ሰው በመግደል፣ ከባድ የአካል ጉዳት በማድረስ፣ የአገር ኢኮኖሚ ለማውደም በመሳተፍ፣ ህገ መንግስቱን በኃይል ለመናድ በመሞከር ወንጀል ያልተሳተፉ ፍርደኞችና ተከሳሾች እንደሆነ ተገልጿል።

በዚሁ መሰረት በፌደራል ደረጃ በሽብር፣ በሁከትና ብጥብጥ፣ በሀይማኖት አክራሪነትና በተለያዩ ወንጀሎች ክሳቸው በሒደት ላይ የሚገኙና የእስር ቅጣት ተላልፎባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙ 417 ታራሚዎች ዛሬ ከማረሚያ ቤት ይወጣሉ።

በተመሳሳይ ጉዳያቸው በህግ በመታየት ላይ የነበሩ 329 ተጠርጣሪዎችም የተሃድሶ ስልጠናውን ጨርሰው ዛሬ እንደሚለቀቁ ገልጿል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s