በድፍን ኦሮሚያ ሰፊ መሰረት ያለው የቤት ውስጥ አድማ ለማድረግ እቅድ እየተነደፈ ነው

በተደጋጋሚ ሲደረግ ከነበረው የጠነከረ የቤት ውስጥ መቀመጥ አድማ በኦሮሚያ በድንገት ሊጠራ እንደሚችል ተሰማ። ከዚሁ አድማ ጋር በተያያዘ ይሁን በሌላ በግልጽ ባይጠቆምም አድማ እንደሚጠራ የኦሮሞ አክቲቪስት ነን የሚሉና በዚሁ ተጋባራቸው የሚታወቁ ፍንጭ ሰጥተዋል። ይህ አገሪቱን እየጎዳ ያለው አድማ የመጨረሻ ግቡ የስርዓት ለውጥ እስካልመጣና ሁሉንም የሚያካትት መድረክ እስኪፈጠር የሚከናወን የሰላማዊ ትግል ስልት እነድሆነም ተጠቁሟል።

አቶ ጃዋር መሕመድ እንዳሉት ነገሮች በዚህ የሚቀጥሉ ከሆነ ከቀድሞው የጠነከረ የትግል ጥሪ ይቀርባል። ቀደም ባሉት ጊዚያት የስርዓቱን የኢኮኖሚ አከርካሪ የሚሰብር ስትራቴጂ እንደሚቀየስ አስታውቀው ነበር። በኦሮሚያ ቄሮዎች -ወጣቶች በሰንሰለት የሚያራቡት መረጃ በፍጥነት የሚዳረስና አድማው አስቸጋሪ በሚባል ደረጃ የሚከናወን መሆኑንን የቀድሞው ተሞክሮዎች አሳይተዋል።

አድማው መቼ እንደሚጀመርና ለምን ያህል ቀን እንደሚቆይ ይፋ አልሆነም። በሳምንቱ ማገባደጃ በሜኖሶታ የአማራና የኦሮሞ ትብብር ያካሄዱት ስብሰባ ከወትሮው በተለይ በስምምነትና የቀድሞውን የልዩነት ዘመን የኮነነ፣ ቀደም ሲል የነበረው እርስ በርስ የመባላት ስልት ጥፋት ሆኖ የተወገዘበት፣ አብዛኛውን ተናጋሪዎች በአማርኛ ንግግር ያደረጉበትና አብሮ ለመስራት ቀደም ሲል ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ስምምነት የተደረሰበት መሆኑ ምን አልባትም ሰላማዊ ተቃውሞውን አድማስ ለማስፋት ያስችላል የሚል ግምት አሳድሯል። ኦህዴድ ፊቱን ወደ ህዝብ ጥያቄ ባዞረበትና የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ በይፋ በጠየቀበት በአሁኑ ወቅት በመላው ኦሮሚያ ሰፊ የተባለ አድማ ለመጥራት መታሰቡ ወጤቱን እንዲጠበቅ አድርጎታል። አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቤት ውስጥ ዘግቶ መቀመጥን ይከለክላል?

በቅርቡ ከእስር የተለቀቁት አቶ በቀለ ገርባ፣ እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌና ሌሎች የኦፍዴን አመራሮች በንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ አግባብ ያልሆነ መሆኑን ጠቅሰው ምክር መለገሳቸው ይታወቃል። 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s