ብዕረኛው ስዩም ተሾመ ታሰረ፤ የት እንደተወሰደ የሚያውቅ የለም – እህት

ስዩም ተሾመ በበሰለ ብዕሩ የሚታወቅ፣ የሚያነሳቸው ጉዳዮች ጠንካራ፣ የብዕር አፎቱ የበረታ፣ ለሚያነሳቸው ሃሳቦች የሰፋ ማስደገፊያ በማቅረብ የሚሟገት፣ በአገር ጉዳይ ተከራካሪ፣ አስተያየት ሰጪ ኢትዮጵያዊ ነው። ስዩም በሚጽፋቸውና በሚያትማቸው ጉዳዮች ሳቢያ የኮማንድ ፓስት አባልት ወዳልታወቀ ቦታ ወስደውታል።

እህቱ ለአሜሪካ ሬዴዮ እንደገለጸችው ቤተስብ የት እንዳለ አያውቅም፤ ማወቅም አልቻለም። የት እንደወሰዱትም ጠይቆ መረዳት አስቸጋሪ ሆኗል። ባልደረባው በበኩሉ ” ምንም ማድረግ አይቻልም” ብሏል። 

በበርካታ ወታደሮች ተከቦ የታሰረው ስዩም ተሾመ ቤቱ ተሰብሮ ብርበራ እንደተደረገበትና ያሉት መረጃዎች በሙሉ እንደተወሰዱበት ኢሳት አመልክቷል። አያይዞም መምህርና የለውጥ አራማጁ ስዩም ተሾመ በመከላከያና በፌደራል ወታደሮች ተከቦ መታሰሩ ቢነገርም ወዴት እንደሄደ ግን የሚታወቅ ነገር የለም።

የስዩም ተሾመ የቅርብ ጓደኞች ለኢሳት እንደተናገሩት የኮማንድ ፖስቱ አባላት በወሊሶ የተካሄደውን አድማ ተከትሎ በርካታ ወጣቶችም እየተሰሩ ይገኛሉ። የአምቦ ዩኒቨርስቲ ወሊሶ ካምፓስ መምህርና በማህበራዊ ድረ ገጽ የለውጥ አራማጁ ስዩም ተሾመ የታሰረበት መንገድ ግን አስደንጋጭ እንደነበር ነው ለኢሳት የደረሱት መረጃዎች የሚያመለክቱት።

የስዩም የቅርብ ጓደኛ እንደሚሉት የኮማንድ ፖስቱ አባላት በሶስት መኪና ሙሉ ተጭነው በቤቱ አካባቢ ከበባ በማድረግ መምህርና የለውጥ አራማጁን አስረው ወስደውታል። ስዩም ተሾመ በመኪና ተጭኖ ሲወሰድ ከማየት በስተቀር ወዴት እንደወሰዱት እንደማይታወቅ የስዩም ተሾመ ጓደኛ ይናገራሉ። እናም አገዛዙ ስዩም ያለንበትን ሁኔታ ሊያሳውቀን ይገባል ነው ያሉት። በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በሚል በርካታ እስረኞች ቢለቅም እንደገና አዲስ የእስር ዘመቻና ዙር መጀመሩን የአካባቢው ምንጮች ይናገራሉ።

በተለይም በኦሮሚያ ላለፉት 3 ቀናት የተካሄደውን አድማ መነሻ በማድረግ የኦሕዴድ ባለስልጣናት ሳይቀሩ እየታሰሩ ነው የሚገኙት። ስዩም ተሾመ በታሰረበት ውሊሶ ከተማ በርካታ ወጣቶች መታሰራቸውንም የስዩም ተሾመ የቅርብ ጓደኛ ለኢሳት ተናግረዋል።

በኦሮሚያ የተካሄደውን አድማ አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ በኢትዮጵያ የቀለም አብዮትን በማካሄድ ስልጣን ለመያዝ የሚፈልጉ ሃይሎች አሉ በማለት የእስር ርምጃ እየተወሰደ መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s