በሸካ ደን በተነሳ ሰደድ እሳት በ200 ሔክታር ላይ የሚገኝ የተፈጥሮ ሀብት ወደመ

በምዕራብ ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ክልል ኢሊባቦራ ዞን ጎሬ ከተማ ወደ ደቡብ ክልል ሸካ ዞን ማሻ ከተማ በሚወስደው መንገድ 14 ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኝ ተፈጥሯዊ ደንና ውኃ አዘል መሬት ላይ ሰደድ እሳቱ ተከስቷል፡፡ ምክንያቱ እስካሁን ባይታወቅም በቦታው ተፈጥሯዊ ደን፣ የጫካ ቡና፣ ኮሮሪማ፣ የማር ቀፎዎችና ውኃ አዘል መሬቶች ይገኛሉ፡፡

የሸካ ዞን የአካባቢ ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ዓለሙ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአጠቃላይ 200 ሔክታር በሚገመት መሬት ላይ የነበሩ ተፈጥሯዊ ሀብቶች ወድመዋል፡፡

‹‹ሰደድ እሳቱ በሰባት ቀበሌዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች፣ የመንግሥት ሠራተኞችና ተማሪዎች ባካሄዱት ርብርብ ተቆጣጥረውታል፡፡ በአሁኑ ወቅት እሳቱ ወደ ሌሎቹ አካባቢዎች መዛመቱን ያቆመ ቢሆንም፣ ሙሉ በሙሉ ግን አልጠፋም፤›› ሲሉ አቶ ታረቀኝ አስረድተዋል፡፡

በምዕራብ ኢትዮጵያ በሸካና በአካባቢው የሚገኙ ሰባት አካባቢዎች ላይ የሚገኝ ተፈጥሯዊ ሀብት በዩኔስኮ ተመዝግቧል፡፡ በሰደድ እሳቱ የወደመው አካባቢ ከሰባቱ አካባቢዎች አንዱ ሲሆን፣ ጠቅላላ ስፋቱ 5,038 ሔክታር ነው፡፡

ሥፍራው የባሮ ወንዝ ሲሞላ የሚተኛበት ስለሆነ ከፊል ውኃ አዘል መሬት ሲሆን፣ ዙርያው ደግሞ በጥቅጥቅ ተፈጥሯዊ ደን፣ በጫካ ቡና በኮሮሪማና በማር ቀፎ የተሞላ ነው፡፡

የመልካ ኢትዮጵያ የሸካ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አዱኛ ሻዌኖ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አካባቢው ቀደም ሲል በዓመት ለአሥር ወራት ዝናብ ይዘንባል፡፡ አሁን ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለስድስት ወራት ዝናብ ያገኛል፡፡

ሰደድ እሳቱ እንዴት ሊከሰት እንደቻለ ለአቶ አዱኛ ጥያቄ ፈጥሮባቸዋል፡፡ ነገር ግን ደኑ ለአካባቢው ሕዝብ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ በኅብረት ወጥቶ ሊቆጣጠረው መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙት ኦሮሚያ ክልል ኢሊባቦር ዞን፣ ጂማ ዞን፣ ጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን፣ ደቡብ ክልል ሸካ ዞን፣ ቤንች ማጅ ዞንና ከፋ ዞን ተፈጥሯዊ ደን ያላቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s