አሜሪካ ለቪዛ ማመልከቻ ማህበራዊ ሚዲያን እንደ መስፈርት ልታደርግ አስባለች

አሜሪካ ወደ አገሯ መግባት ለሚፈልጉ እያንዳንዱ ተጓዦች የቪዛ ማመልከቻ ለመስጠት የማህበራዊ ሚዲያን የኋላ ታሪክ አጠቃቀምን እንደ መስፈርት ልትጠቀም ትችላለች ተባለ፡፡

እቅዱ የፌስቡክና የትዊተር ዝርዝር መረጃዎችን ተጓዦች እንዲያቀርቡ ይፈልጋል የተባለ ሲሆን÷ በዓመት የ14 ነጥብ 5 ሚሊየን አመልካቾችን እንደሚመለከት ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም አመልካቾች የአምስት ዓመታት የጎዞ ታሪክ፣ የስልክ ቁጥር እና የኢሜል አድራሻ እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ ተብሏል፡፡ እንዲሁም ከዚህ ቀደም ከሀገር ከተባረሩ እና በሽብር ድርጊት የተሳተፈ ዘመድ ካላቸው ማሳወቅ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡

አዲሱ እቅድ ከአሜሪካ ጋር የነጻ ቪዛ ዝውውር ስምምነት ያላቸው አገሮችን እንደ ብሪታንያ፣ ካናዳ፣ ጀርመንና ፈረንሳይን አይመለከትም ተብሏል

ከፍተኛ ኃላፊዎች አዲሱን እቅድ ጽንፈኞችን ለመለየት እንደሚረዳ አስታውቀዋል፡፡ የማህበራዊ ሚዲያ 14 ሰዎች ከሞቱበት የ2015ቱ የካሊፎርኒያ ጥቃት ጀምሮ በተለየ ሁኔታ አጽንዖት ሰጥተው እየመረመሩ ሲሆን÷ ከፍተኛ ኃላፊዎች የጥቃት አድራሹን የመልዕክት ልውውጥ ማየት ያለመቻላቸው ለአደጋው መፈጠር ምክንያት ነው ይላሉ፡፡

ምንጭ ፋና ቢቢሲን ጠቅሶ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s