የሶማሊው ፕሬዚዳንት አንቀጽ 39ን ተግባራዊ አደርገዋለሁ እያሉ በመዛት ላይ ናቸው

ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ ደስተኛ ያልሆኑት የህወሃቱ ቀኝ እጅ አቶ አብዲ ሙሃመድ ኡመር የህገ መንግስቱን አንቀጽ 39ን በመጥቀስ የመገንጠል ጥያቄ አቀርባለሁ በማለት እየዛቱ ነው።

አዲስ አበባ ውስጥ የነበሩ የክልሉ አገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም ፖለቲከኞች ወደ ጅጅጋ የተጠሩ ሲሆን፣ የልዩ ሃይል አዛዦች፣ የልዩ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮችና የህወሃት ጀኔራሎች ጌሪ ጎአን በተባለ ስፍራ ላይ ሚስጢራዊ ስብሰባ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

በአካባቢው የስልክ መስመር እንዲቋረጥ መደረጉንም ምንጮች ገልጸዋል። አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ወደ ጅጅጋ በማምራት በአካባቢው የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ እንደሚሄዱ ምንጮች ገልጸዋል። በዶ/ር አብይ የሹመት ስነስርዓት ላይ ተገኝተው የነበሩት አቶ አብዲ ደጋግመው ስለ አልሸባብና በአካባቢው ስላሉ ታጣቂዎች በማንሳት በክልሉ ስጋት እንደተፈጠረ አድርገው ይናገሩ እንደነበር የገለጹት ምንጮች፣ ከእርሳቸው ጋር የፌዴሬሽን ም/ቤት ሰብሳቢና የደህንነት ሰራተኞች አብረዋቸው ነበሩ።
በእለቱ ከፍተኛ የመረበሽ ስሜት ይታይባቸው የነበሩት አቶ አብዲ ኢሌ ወደ ጅጅጋ እንደተመለሱ፣ አዲስ አበባ የሚገኙ ባለስልጣኖቻቸውንና የአገር ሽማግሌዎቻቸውን መርጠው ምክር እንደጀመሩ ታውቋል።

በአቶ አብዲ ኢሌ ቁጥጥር ስር የሚገኘው ካካራ ኒውስ የተባለው ሚዲያ ዶ/ር አብይ የኦነግ አባል መሆናቸውን ዘገባ ይዞ ከወጣ በሁዋላ ዘገባውን እንዳነሳ ታውቋል። ኦነግ የአገሪቱን ስልጣን ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ የገለጸው ዘገባው፣ በዚህም ምክንያት የሶማሊ ክልል ድንበሩን ለማስከበር አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ ጠቅሶ ነበር። ዶ/ር አብይ በጅግጅጋ ጉዟቸው ምን አይነት ውሳኔ እንደሚያሳልፉ ባይታወቅም፣ ጅግጅጋን ለመጎብኘት መዘጋጀታቸው በአካባቢው ያለው ችግር አሳሳቢ መሆኑን የሚያመለክት ነው።

ኢሳት ትናንት ባወጣው ዘገባ ህወሃት በኢትዮ-ሶማሊ በኩል ያለው ሰላም በታጣቂዎች እየደፈረሰ መሆኑንና አቶ አብዲ ኢሌ ከሌሉ ክልሉ ሰላም እንደማያገኝ ለማሳመን ሙከራ እያደረገ መሆኑን ጠቅሶ ነበር። አቶ አብዲ ኢሌ በስልጣን ላይ እንዲቆዩ ከተደረጉ በሁዋላ፣ ኢትዮ-ሶማሊያውያን በፌደራል መንግስቱ ስልጣን በቂ ውክልና የላቸውም በሚል እስከ 5 የሚደርሱ የሚኒስትር ቦታዎችን በማሰጠት፣ ህወሃትና ሶህዴፓ ከአህዴድና ብአዴን ሊገጥማቸው የሚችለውን ተቃውሞ ለመቋቋም ማቀዱን መዘገባችን ይታወቃል።

(ኢሳት ዜና መጋቢት 27 ቀን 2010 ዓ/ም)

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s