አብይ አህመድ 25 ሺህ ከሚሆኑ ወገኖች ጋር ሊወያዩ ነው

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ 25 ሺህ ከሚሆኑ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በነገው ዕለት በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚወያዩ ፋና የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ጠቅሶ ይፋ አደረገ።

የህዝብ ውይይቱ “የፍቅር እና የአንድነት ኪዳን” በሚል መሪ ቃል በነገው ዕለት እንሚካሄድ ነው የመንግስት ኮሙዪኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ የተናገሩት።

ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይት ቃለመሀላ በፈፀሙበት እለት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ባሰሙት ንግግር መጠነ ሰፊ የሪፊርም እርምጃዎችን ለማካሄድና የህዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ ቃል በገቡት መሰረት የሚካሄድ ውይይት እንደሆነ ከፅህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። 

ህዝባዊ ውይይቱ አንድነትን፣ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን፣ ልማትን እና የመልካም አስተዳደር ሥርዓትን ለማጎልበትና ከህዝብ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት እንደሚረዳ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ የፌዴራል፣ የክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ምሁራን እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ተወካዮች ይሳተፋሉ ተብሏል።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s