አቶ ሃይለማሪያምና ጃዋር መሐመድ መደራደራቸው ተሰማ

ከሃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ሲያበስሩ ” ዝርዝሩን ለፓርላማ አቀርባለሁ” ካሉ በሁዋላ በዝምታ ያለፉት አቶ ሃይለማሪአም ደሳለኝ ከኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሐመድ ጋር መደራደራቸው ተሰማ። ድርድሩ በፈተና መሰረቅ ጉዳይ ላይ እንደሆነ ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ ገልጸዋል።

የአሜሪካ የዛጎል ተባባሪ እንደዘገበው አቶ ሃይለማሪያምና አቶ ጃዋር የተነጋገሩት በስልክ ነበር። አነጋጋሪው አሜሪካዊ ሲሆኑ የተነጋገሩበት ጉዳይ የማትሪክ ፈተና በድጋሚ እንዳይሰረቅ የነበረውን ፍርሃቻ ተከትሎ ነው። የአደራዳሪ ሚና የተጫወቱት ሰው አቶ ጃዋርን ለማስፈራራት ሞክረው እንደነበር፣ ይሁን እንጂ አቶ ጃዋር ሃይለቃል በመናገር ሲያስደነግጧቸው አቶ ሃይለማሪያም አቶ ጃዋርን ገስጸዋቸዋል።

በወቅቱ የሁለተኛ ደረጃ ፈተና ተሰርቆ የነበረ መሆኑ የፈተናው ጊዜ በመቀየሩ የተፈጠረውን የቁሳዊ፣ የስነልቦናዊና አጠቃላይ የጊዜ መዛባት፣ ዳግም የተዘጋጀው ፈተናም ተሰርቋል በሚል ከፍተኛ ስጋት በተማሪዎች ዘነድ በመፈጠሩ ነበር ንግግር ማድረግ የተፈለገው። በንግግሩ የአቶ ጃዋር አቁዋም ምን እንደነበር በዝርዝር ባይታወቅም ለተማሪዎች የመዘጋጃ ጊዜ እንዲሰጥ በተጠየቀው መሰረት መፈቀዱ አይዘነጋም። በጉዳዩ ዙሪያ አቶ ጃዋርን ለማግኘት ተባባሪያችን ሞክሮ አልተሳካለትም።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s