Advertisements

“ግርማ ሰይፉ በኢህአዴግ ድጋፍ መመረጣቸውን በደህንነት ስብሰባ ላይ ሰምቻለሁ”

” ብቸኛ የፓርላማ  ተመራጭ ” በሚል ስያሜ የሚታወቁት አቶ ግርማ ሰይፉ በኢህአዴግ ይሁንታ እንዲመረጡ መደረጉን ቀደም ሲል በመረጃና ድህንነት ውስጥ በተለያዩ ሃላፊነቶች ከሃያ ዓመት በላይ ማገልገላቸውን የሚናገሩት አቶ አያሌው መንገሻ ተናገሩ።

ይህን የሰሙት ከክፍል ሃላፊ በላይና በውጭ ጉዳይ ሃላፊዎች ስብሰባ ላይ መሆኑንን አመልከተዋል። አቶ አያሌው እንዳሉት በዚሁ ስብሰባ ላይ ኢህአዴግ ደግፎና ፈቅዶ አቶ ግርማ እንዲመረጡ ያደረገው ” የእኛ የድርጅት አባል ከሆኑት በላይ ለእኛ ስለሚጠቅመን ነው” በማለት ዶክተር ደብረጽዮን ሲናገሩ በስብሰባው ላይ ነበሩ። ዘጠና ዘጠኝ ከመቶ ኢህአዴግ ባሸነፈበት የምርጫ ዓመት፣ ቢፈለግ ሙሉ በሙሉ መጠቅለል ይችል እንደነበር፤ ይህ ያልተደረገው ግን አቶ ግርማ ከአንድ የድርጅት አባል እኩል ኢህአዴግን እንደሚጠቅሙ በመታመኑ ነው።

በዚሁ መነሻ ” አቶ ግርማ ሰይፉ ከኢህአዴግ የተለየ አመለካከት የሌለው ሰው ነው” ሲሉ ያጠቃለሉት አቶ አያሌው ይህንን የተናገሩት ከህብር ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው። አቶ አያሌው ይህን ያሉት በሙሉ መረጃ ተደግፈው እንደሆነም አመልክተዋል። አቶ ግርማ ሰይፉ ለአንድ የምርጫ ዘመን በፓርላማ ማሳለፋቸው የሚታወስ ነው።

Advertisements

Zaggolenews. የዛጎል ዜና

Editor of zaggolenews.com contact editor - zaggolenews2016@gmail.com

You may also like...

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: