የለገደንቢ ሚድሮክ ወርቅ ጉዳይ ዓለም ዓቀፍ አጀንዳ እንዲሆን እየተሰራ ነው፤ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎች ጥናት እያደረጉ ነው!!

” ጉዳዩ በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ አሰቃቂ ወንጀል በመሆኑ ዓለም ዝም የሚለው አይሆንም ” በማለት ለዛጎል አስተያየታቸውን የሰጡ አንድ ተቆርቋሪ ” ባለሃብት የሚባሉት ሰው ብቻ ሳይሆኑ ይህንን ሁሉ ሰብአዊ ቀውስ እያየ ዝምታን የመረጠው መንግስትም የሚጠየቅበት አግባብ እየትሰራበት ነው” ብለዋል።

ከፋብሪካው በሚወጣ ተረፈ ምርት የደረሰው ቀውስ ያማል። ከሁሉም በላይ ህጻናት መዳህ አቅቷቸው አፈር አየቃሙ ሲንደባለሉ እያዩ፣ ሰውነታቸው የተፈጥሮ ስርዓቱን በመሳቱ ሳቢያ የደረሰውን ጉዳት እያስተዋሉ፣ እናት ከእርግዝና ጀምሮ በስቃይ፣ ጽንስ እየተጨኛገፈባት፣ ወልዳም ቢሆን ያሰበችውን አድጎ የሚቦርቅ ልጅ ማየት ተስኗት፣ የአካባቢው ስነ ውበት ረግፎና ወሃ ተበክሎ…. ይህ ሁሉ ሆኖ የመንግስት ሃላፊዎች ” ፋብሪካው የሚገለገልበት ኬሚካል ችግር የማያመጣ መሆኑንን አረጋግጠናል” ማለታቸው አብዛኞችን ያሳዘነ የሰሞኑ አብይ ጉዳይ ነው።

Image result for midroc gold victimesImage result for midroc gold victimes

 

ከዛሬ አስርና አስራ አንድ ዓመት በፊት ሪፖርተር ጋዜጣ የለገደንቢን የወርቅ ማምረቻ አስመልክቶ በተፈጥሮና በሰው ልጆች ላይ ከፍተኛ አደጋ እየደረሰ መሆኑንን ከክልሉ ተቆርቋሪ ሃላፊዎች በደረሰው መረጃ መሰረት ቦታው ድረስ ሪፖርተር በመላክ ሪፖርት አቅርቦ ነበር። በወቅቱ በፋብሪካው ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኛችን ጭምሮ ነዋሪዎች  ” አደጋው ወደፊት እየከፋ ይሄዳል። ሰፊ የማስፋፊያ ቦታ እያካለሉ ስለሆነ፣ ጉዳቱም የዛን ያህል ይሰፋል” ብለው ነበር።

ይህ ብቻ ሳይሆን የወርቅ ማምረቻው ወደ ሚድሮክ የተዛወረበት አካሄድ የተጭበረበረ፣ የወርቅ ማምረት ሂደቱ ቁጥጥር የማይደረግበት፣ አሰራሩ በርካታ ግድፈት ያለበት እንደሆነ በመጥቀስ በተደጋጋሚ ዘገባዎች በሪፖርተር ጋዜጣ ሲታተሙ ነበር። በወቅቱ ከሚመጡት መረጃዎች ብዛት በየቀኑ የሚታተሙት ጉዳዮች የህዝብ ቀልብ በመሳባቸው በአዘጋጆቹ ላይ ” በሚድሮክ ወርቅ የመጣ ” በሚል ህይወት ላይ ያነጣጠረ ማስፈራሪያ ይፈጸም ነበር። የግድያ ሙከራም ተደርጓል። 

በወቅቱ መረጃዎች ይፋ ሲሆኑ እርምጃ ተወስዶ ቢሆን ኖሮ  ዛሬ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት መቀነስ በተቻለ በሚል ቁጭት ጉዳዩን በጨረፍታ አነሳነው እንጂ በጉዳዩ ላይ ሪፖርተር ውስጥ የነበረው  ፍትጊያ ወደፊት በስፋት የሚባልበትና እንደ ታሪክ የሚቀመጥ ታላቅ ጉዳይ ነው።  

ጉዳዩ ወደ ህግ እንደሚሄድ የገለጹት ክፍሎች ለዛጎል እንዳሉት “ከወርቅ ማምረቱ ጋር በተያያዘ የደረሰው ጉዳት የዓለማችን አስነዋሪና አስከፊ ወንጀል ነው፤ መንግስትን ጨምሮ ወደ ህግ የማቅረቡ ስራ በቅርቡ ይፋ ይሆናል። ባለሃብቱ ከእስር ባይወጡ እንኳን ባሉበት የሚጠየቁበት አካሄድ አለ” ብለዋል። 

ሕዝብ የኤኤክትሪክ ሃይል እንዲቋረጥ ካደረገ በሁዋላ የለገደንቢ ወርቅ ማምረት ስራ እንዲቋረጥ መደረጉን ፋናን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s