« ለአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) መስራች አባላት እንኳን ደስ ያላችሁ!» መዐሕድ

የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) ራዕይ የአማራ ህዝብ ጸረ አማራ የሆነ ማንኛውም ህዝባዊ ጥቃት በመመከት በመላው ኢትዮጵያ ተንቀሳቅሶ የመኖር፣ ሀብትና ንብረት የማፍራት መብቱ ተከብሮ፤ የማንነት ክብሩና ልዕልናው ተረጋግጦ፤ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞቹን ያለገደብ ተጠቅሞ እንዲሁም ለደረሰበት የሰብዓዊና ስነልቦናዊ በደል ተገቢውን ፍትህ አግኝቶ ሲኖር ማየት ነው።

በመሆኑም ለአማራ ህዝብ ህልውና የሚታገልና ለህዝባችን ሁሉን አቀፍ ጥቅም ጥብቅና የሚቆም ማንኛውም ድርጅት የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት አጋር ነው። የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምስረታ ሂደትን የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት አባላትና አመራር አካል በንቃት ሲከታተለው የቆየ ጉዳይ ነው። በምስረታው ሂደት ላይ የተሳተፋችሁ ወገኖች ጥረታችሁ ፍሬ አፍርቶ ዛሬ የምስረታ ብስራቱን ሰምተናል።

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ለአማራ ህዝብ ህልውና የሚታገልና ሁሉን አቀፍ ጥቅሞቹን ለማስከበር የሚታትር እንደሚሆን ባለ ሙሉ ተስፋዎች ነን። የተነጠቁ የአማራ ጥንተ ርስቶችን (ወልቃይት፣ ራያ አዘቦ፣ መተከል፣ በረራ እና የመሳሰሉትን) በማስመለስና አማራው የተቀማውን የዜግነት ክብር መልሶ ለማጎናፀፍ በሚያደርገው ትግል የጎላ ድርሻ እንደሚኖራችሁም አንጠራጠርም። የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) የህዝባችን ሁለንተናዊ ጥቅም በሚያስከብር መልኩ ማንኛውንም አይነት ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን!
መልካም የሥራ ዘመን ይሁንላችሁ!

አንድ አማራ ለሁሉ አማራ ሁሉ አማራም ለአንድ አማራ!

የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ)

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s