ከአዲስ አበባ ግብረ ሀይል የቅዳሜውን ህዝባዊ ሰልፍ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

ቅዳሜ ሰኔ 16 የሚካሔደውን ህዝባዊ ሰልፍ በተመለከተ ግብረ ሀይላችን በሰልፉ አዘጋጅ ኮሚቴዎች የተገለፀውን”ዴሞክራሲን የማወደስ” አላማ የሚደግፈው መሆኑን እየገለፅን ህዝባዊ ሰልፉም አሁን በዶ/ር አቢይ የተጀመረው የለውጥ ጭላንጭል እንዲቀጥል የለውጥ ሀይሉን ከመደገፍ ባሻገር የለውጡን ቀጣይነት የሚያረጋግጡ ህዝባዊ ጥያቄዎችም የሚንፀባረቁበትና ኢትዮጵያዊ አንድነት የሚንፀባረቅበት በሰላም ተጀምሮ በሰላም የሚጠናቀቅ ሰልፍ እንዲሆን የበኩሉን ጥረት እንደሚወጣ በአፅንኦት እንገልፃለን በሰልፉ እለትም ከድጋፍ ባሻገር

— ለዛሬው የለውጥ ጅምር ላለፉት አመታት የህይወትና የአካል መስዋእትነት የከፈሉ አካላት የሚወደሱበት

— የለውጥ ጅምሩ ቀጣይነት እንዲኖረው ወሳኝ ጉዳይ የሆነው የመሠረታዊ ተቋማት ግንባታ እንዲጀመር ጥያቄ የሚቀርብበት

— በዜጎች ላይ ተፅእኖ የሚያሳድሩ አፋኝ አዋጆች እንዲሻሩ የሚጠየቅበት

— በክልሎችና በህዝቦች መካከል ግጭት የሚፈጥሩ የህገ መንግስቱ አንቀፆች እና የመንግሰት መዋቅር እንዲሻሻል የሚጠየቅበት

— በዜጎች ላይ ግድያ የአካል ማጉደል፣ የመብት ጥሰት የፈፀሙና የህዝብ ሀብት የመዘበሩ የመንግስት አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚጠየቅበት

— ዜጎችን ለዘመናት ከኖሩበት ቀዬ ማፈናቀልና በጎሰኝነት አስተሳሰብ መጨቆን በአስቸኳይ እንዲቆም የሚጠየቅበት

— አሁን በተለያዩ ክልሎች እየተካሔዱ ላሉ የብሔር ግጭቶችና የዜጎች ግድያዎች አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸውና አጥፊዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚጠየቅበት

እንደሚሆን በማመን ከሰልፉ ዋዜማ ጀምሮ በቅስቀሳውና በእለቱም በህዝባዊ ሰልፉ ላይ በንቃት እንደምንሳተፍ እንገልፃለን

ድል ለዲሞክራሲ
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s