ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ ሙሉ መግለጫ

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ክቡር ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድን ለመደገፍ በተካሄደው ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የተፈጸመውን የሽብር ድርጊት በጽኑ ያወግዛል። በዜጎቻችን ላይ ለደረሰው ጉዳት የተሰማዉን ጥልቅ ሃዘን ይገልጻል።

ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ የኢፌዲሪ ጠ/ሚኒስትር በሆኑበት በጥቂት ወራት ውስጥ የጀመሩትን ተስፋ ሰጪ የለዉጥ እንቅስቃሴ ለመደገፍ እና ለማመስገን በፊንፊኔ መስቀል አደባባይ በተዘጋጀዉ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ከፊንፊኔ እና አካባቢው የመጡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ታድመውበታል።

በዚህም በአገራችን ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች የአገሪቱ መሪ የጀመራቸውን የለውጥ እንቅስቃሴዎችን በአዎንታዊነት በመቀበልና አጋርነታቸውን ለመግለጽ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል።

ሰላማዊ በነበረው የድጋፍ ሰልፍ የአገሪቱን አንድነትና መንግስት የጀመራቸውን ሁለንተናዊ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን የሚያወድሱ መልዕክቶችን ባነገቡ የድጋፍ ሰልፈኞች ለመሪያቸው ያላቸውን ድጋፍና አጋርነት እየገለጹ በሚገኙበት ደማቅ ስነ ስርዓት ላይ የጥፋት ሀይሎች ባደረሱት የቦንብ ጥቃት በንጹሐን ዜጎቻችን ላይ ጉዳት ደርሷል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በንጹሐን ዜጎቻችን ላይ የተፈፀመውን የሽብር ድርጊት በጽኑ ያወግዛል። በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን እና ለመላው የኢትዮጽያያ ሕዝብ መጽናናትን ይመኛል።ከዚህ በተጨማሪም ክቡር ጠ/ሚኒስትሩ የጀመሯቸውን የለውጥ እንቅስቃሴዎች ለመደገፍና የጥፋት ሀይሎችን እኩይ ተግባር ለመመከት ክልሉ በማናቸውም ጊዜ ከጎናቸው የሚቆም መሆኑን ያረጋግጣል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s