የፖሊስ አመራሮች፣ ተጨማሪ መሳሪያና ድርጊቱን የፈጸሙ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው

የክፋት ሃይሎች በጠነሰሱት የክፋት ሴራ የተነሳ በዛሬው እለት በመስቀል አደባባይ በደረሰው ፍንዳታ የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ 9 የአዲስ አበባ እና የፌዴራል ፖሊስ አመራሮች እና አባላት ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ ታወቀ።

የመንግስት ኦፊሳል ድረ ገጾች እንዳስታወቁት በተጠቀሱት አካላት ላይ ምርመራ የሚደረገው  ከተፈጸመው “የሽብር ጥቃት “ጋር በተያያዘ ባሳዩት ክፍተት ነው። ድረ ገጾቹ የታሰሩትን ስም ዝርዝር አልጠቀሱም።

ዶክተር አብይ ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ፈጽመዋል የተባሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ራስዋን የሳተች የአእምሮ በሽተኛ የሚመስሉ ሁለት ሴቶች፣ አንድ መታወቂያው የቤተ ክህነት ሰራተኛ መሆኑን የሚያረጋግጥ ጎልማሳን ጨምሮ በጥቅሉ አምስት ሰዎች መያዛቸው ታውቋል። አንድ በቅርብ እርቀት ሆኖ አንዷን ሴት ሲከታተል የነበረ ለመንግስት ቴሌቪዥን እንዳለው ሴትየዋ ዳግም ለማፈዳት በዝግጅት ላይ ነበረች፣ በያዘችው ከረጢት ውስጥም ተጨማሪ በስም ያልጠቀሰው መሳሪያና ተቀጣጣይ ፈንጂ ተይዞባታል።

Image may contain: 3 people, people standing and outdoor

ከአስከፊው አደጋ በሁዋላ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ድርጊቱ የተጠናና ሆን ተብሎ በባለሙያዎች የተቀነባበረ ሲሉ ነው ድርጊቱን የገለጹት። አያይዘውም ምርመራ ሲልያልቅ ጉዳዩ ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን አመላክተዋል።

ዛሬ የተለያዩ የአገር ውስጥ ሚዲያዎች እየተቀባበሉ ሲያሰራጩት የነበረው የህዝብ ማዕበል፣ የቀድሞ አስተሳሰብና አካሄድ ላይመለስ ማክተሙን የሚያረጋግጥ እንደሆነ የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች በመንግስት ሚዲያ ሲናገሩ ተሰምቷል።

ድርጊቱን የተለያዩ አገራት፣ ክልሎችና አስተዳደሮች ኮንነውታል። ኤርትራ አጥብቃ እንደምታወግዝ ይፋ አድርጋለች። አሜሪካም ድርጊቱን በማውገዝ አገሪቱ በተሳካ የለውጥ ጉዞ ውስጥ እያለች ይህ መሆኑ ተቃውማለች።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s