ታላቁ አንዋር መስጊድ ከእሳት ቃጠሎ ተረፈ

ትናንት ረቡዕ ሌሊት ለሐሙስ አጥቢያ በታላቁ አንዋር መስጊድ የተነሳው የእሳት አደጋ በመስጊዱ ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ሥር ውሏል። ኾኖም በመስጊዱ ዙርያ የሚገኙ ሱቆች ከነንብረቶቻቸው በከፋ ሁኔታ ወድመዋል።

እሳቱ ጉዳት ያደረሰው በተለምዶ “የሴቶች በር” በሚባለው የአንዋር መስጊድ በር፣ “ሄኒፔኒ ካፌ” ከሚገኝበት ከቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ከአስፋልት ማዶ ነው።

ከሴቶች በር አንስቶ የቂቤ መሸጫ ሱቆች፣ አባያ፣ ሂጃብና ሌሎች ኢስላማዊ አልባሳት መሸጫዎች እንዲሁም በተለምዶ “ጎንደር በረንዳ” በሚባለው ሰፈር ያሉ ሱቆች ላይ እሳቱ ጉዳት አድርሷል። ጎንደር በረንዳ በብዛት የሲዲና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች መሸጫ መደብሮች ተሰድረው ያሉበት ገበያ ነው።

መስጊዱን ታኮ የሚገኘው ዑመር ሰመተር ትምህርት ቤት በእሳቱ ጉዳት እንዳልደረሰበት የዐይን እማኞች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ትምህርት ቤት ከቆርቆሮ የተነሱ በርካታ ክፍሎች ያሉት ሲሆን እሳቱ ወደዚያ ቢዛመት ከዚህም የከፋ ጉዳት ይደርስ እንደነበር ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ከሱቆቹ ባሻገር የመስጊዱ የሴቶች በር መግቢያ ቅጥር ውስጥ የሚገኙ የስብከት (ዳዕዋ) አገልግሎት የሚሰጡ የመንፈሳዊ ትምህርት መማሪያ ክፍሎች (መድረሳ) ጣሪያቸው እንደነደደ በእሳት ማጥፋቱ ላይ ተሳትፎ ያደረጉት የዐይን እማኝ አቶ ሙክታር መሐመድ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከንብረት መውደም ሌላ በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት አለመድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን መኮንን ለቢቢሲ ገልጸዋል። በአደጋው የወደሙት ሱቆች በቁጥር 50 እንደሚደርሱም ተገልጿል።

በአካባቢው የነበሩት የኤሌክትሮኒክስ፣ የጨርቃጨርቅ፣ የማርና የቅቤ መሸጫ ሱቆች እሳቱን በከፍተኛ ፍጥነት በማቀጣጠላቸው አደጋውም ቶሎ ሊዛመት እንደቻለ አቶ ሰለሞን ተናገረዋል።

በመጨረሻም በአካባቢው ኅብረተሰብ እና በ 112 የእሳት አደጋ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ትብብር ዛሬ ንጋት ላይ እሳቱ በቁጥጥር ሥር ውሏል ብለዋል። የአደጋው ትክክለኛ መነሻና ያደረሰው ጉዳት ገና በመጣራት ላይ ነው።

ቢቢሲ አማርኛ ፎቶ ቢቢሲ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s