ኦነግ ጊዚያዊ የተኩስ አቁም አወጀ- የሰላም ድርድሩን አደነቀ

ኦነግ የተኩስ ማቆም አዋጅ ማወጁን ያረጋገጠው ለሰላም ንግግሩ ከሰጠው ትኩረትና ከወይይቱ ፍሬ እንደሚገኝ በማመን ነው። በዚሁ መሰረተ ጊዚያዊ የተኩስ ማቆሙ የተጀመረውን ድርድር ተስፋና አገሪቱ የጀመረችው የሰላምና የፍቅር አቅጣጫ እንደሚደግፍ ተመልክቷል። የክልሉ መስተዳድርም ሆነ የፌደራል መንግስት ሁሉም ወገኖች ወደ ሰላም ድርድሩ እንዲገቡ መጠየቃቸው ይታወሳል።

ፋና ዜና – የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተጀመረውን የሰላም ውይይት ለማሳካት ግዜያዊ የተኩስ አቁም ማወጁን አስታወቀ። ግንባሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፥ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን የፖለቲካ ችግር በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንዲበጅለት እንደሚፈልግ ገልጿል።

በቅርቡ በግንባሩ ሊቀ መንበር በሚመራ የኦነግ የልዑካን ቡድንና በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መካከል በተደረገ ውይይት ያለውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሲደረግ የነበረው ጥረት የሚያበረታታ ነው ብሏል።

በመንግስት እና በግንባሩ መካከል የተጀመረውን የሰላም ንግግር መንግስታት፣ ህዝቦችና ሰላም ወዳዶች የሚሹት መሆኑን እንደሚገነዘብም ግንባሩ ገልጿል።

የተጀመረውን የሰላም ንግግር ወደፊት ለማራመድና ለማሳካት ይረዳል በሚል እምነት በጊዜያዊነት ተኩስ ማቆሙን በመግለጫው አስታውቋል። ለጊዜው ይህ የተኩስ ማቆም አዋጅም የተጀመረው ንግግር የሚጠበቀውን ፍሬ ያገኛል ብሎ እንደሚያምንም ገልጿል

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s