“መለስ ዜናዊን ከሞት የማስነሳት ብቃት አለኝ- ተነስቶ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር “ይደመራል” ፓስተር እስራኤል ዳንሳ

በኢትዮጵያ ፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ዘንድ ዝናን እያተረፈ የመጣው ፓስተር/ሰባኪ እስራኤል ዳንሳ ሐዋሳ በተካሄደ ጉባኤ ላይ ነው መለስ ዜናዊን ከሞት የማስነሳት ብቃት እንዳለው የገለጸው። የሚከተለው ኢትዮጵያውያን በፌስቡ ገጻቸው ላይ እየተቀባበሉት ያሉት ዜና ነው:

ይሄን የተናገረው እስራኤል ዳንሳ ሐዋሳ ላይ በነበረው አገልግሎት ላይ ነው። እስራኤል ዳንሳ እንዳለው ከሆነ “የ6 አመቱን ሬሳ መለስ ዜናዊን ከሞት የማስነሳት መንፈሳዊ ብቃት ላይ እገኛለሁ። ሰውን ማስነሳት ለኔ አዲስ አይደለም ከዚህ ቀደምም ሁለት የሞቱ ህጻናትን አስነስቻለሁ” ሲል ከሞት የማስነሳት ልምድ እንዳለው በኩራት ተናግሯል።

እስራኤል ዳንሳ ይቀጥልና “ዋናው በጌታ በኢየሱስ ማመን ነው።የስንፍጭ ቅጣት ታክል እምነት ያለው ሰው የኪሊማንጆርን ተራራ ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት ይቻላል ወይንም አዲስአበባን ወደ ሐዋሳ ሐዋሳን ወደ አዲስአበባ መቀያየር ይቻላል፤ ጌታ ኢየሱስም ይሄን ቃል አስተምሯል”ሲል ነው ለታዳሚው የገለጸው። ታዳሚውም “ይቻላል”በማለት በጭብጨባ አጅቦታል።

እስራኤል ዳንሳ ይቀጥላል “ወ/ሮ አዜብ መስፍን የመለስ መቃብር እንዲቆፈር ከፈቀደች ካለምንም ክፍያ አስነሳዋለሁ፤ ከኔ የሚጠበቀው በጌታ በኢየሱስ ሥም ብቻ መጸለይ ነው” ብሏል። በርግጠኝነትም ከመቃብሩ እንደ አልዓዛር ተነስቶ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር “ይደመራል” ሲል ነው የጌታ የኢየሱስን ስምን እየጠራ የተናገረው።

አንድ ታዳሚ ይሄ ነገር በወለጋ ቄሌም ወረዳ ተሞክሮ እንደከሸፈና ውርደት እንዳያመጣ ሲጠይቀው “እሱ ሐሰተኛ ነው። ከሐሰተኞች ሰዎች መጠንቀቅ አለባችሁ። በኛ ስም የሚነግዱ ብዙ ሐሰተኞች እንደተነሱ እያየን ነው” ሲል መልሶለታል።

የቀድሞው አምባገነን የኢትዮጵያ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በእስራኤል ዳንሳ አማካኝነት ከሞት ይነሳል ብለው ስጋት የገባቸው ሰዎች ይሁንና ከተነሳ በኋላ ይደመራል በመባሉ ተጽናንተዋል።

ECADF

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s