15 አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትርስት ፈንድ አማካሪ ምክር ቤት ተመሰረተ

(EBC) — ከተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ጭምር ልምድና የዳበረ ተሞክሮ ያላቸው ስመ ጥር ኢትዮጵያዊያንንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ያካተተ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትርስት ፈንድ አማካሪ ምክር ቤት ተመሰረተ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በምክር ቤቱ ውስጥ የተካተቱት አባላት ለወሰዱት ተልዕኮ ምስጋና በማቅረብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ተናግረዋል፡፡

የትረስት ፈንዱ አማካሪ ምክርቤቱ አስራ አምስት አባላት አሉት፡፡ በተመድ የልማት መርሃ ግብር፣አለም ባንክ፣ አፍሪካ ልማት ባንክ ፣ በአለም አቀፍ ዪኒቨርስቲዎች፣ በአለም አቀፉ የአዕምሯዊ ንብረት ድርጅት፣በአለም አቀፍ ኩባንያዎች ከፍተኛ ቦታዎች ላይ ያሉና ዕውቅና ያላቸው የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች በምክር ቤቱ አባልነት ተካተዋል፡፡

የካሊፎርኒያው ዩኒቨርሲቲ ምሁር ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሲሆኑ፣የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎቹ ታማኝ በየና እና ኦባንግ ሜቶም በአባልነት ተካተዋል፡፡

የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ከዲያስፖራው ማህበረሰብ በሚገኝ መዋጮ በኢትዮጵያ የሚታዩ ማህብረሰባዊ የልማት ክፍትቶችን ለመሙላት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሀሳብ ጠንሳሽነት ከወር በፊት መጀመሩ ይታወሳል፡፡

አማካሪ ምክር ቤቱም ይህን እቅድ ስኬታማ ለማድረግ ትግብራውን የመቆጣጠርና አቅጣጫ የማስያዝ ተልዕኮ ተሰጥቶታል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s